ሐዋርያት ሥራ 7:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የግብጾችን ጥበብ ሁሉ ተማረ፤ በቃሉና በሥራውም የበረታ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም የግብፆችን ጥበብ ሁሉ ተማረ፤ በንግግሩና በተግባሩም ብርቱ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም የግብጻውያንን ጥበብ ሁሉ ተማረ፤ በቃሉና በሥራውም የበረታ ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም የግብፅን ጥበብ ሁሉ ተማረ፤ በሚናገረውና በሚሠራውም ሁሉ ብርቱ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም የግብፆችን ጥበብ ሁሉ ተማረ፥ በቃሉና በሥራውም የበረታ ሆነ። |
የጣኔዎስ አለቆች ፍጹም ሞኞች ናቸው፤ ፈርዖንን የሚመክሩ ጥበበኞች ምክራቸው እርባና ቢስ ይሆናል። ፈርዖንን “እኛ የጥበበኞች ልጆች የቀደሙም ነገሥታት ልጆች ነን” እንዴት ትሉታላችሁ?
እርሱም “ምንድነው?” አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ ነው፤