ሐዋርያት ሥራ 3:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያንም ነቢይ የማትሰማው ነፍስ ሁሉ ከሕዝብ ተለይታ ትጠፋለች፤’ አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያን ነቢይ የማትሰማ ነፍስ ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይታ ትጥፋ።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያን ነቢይ የማይሰማ ሁሉ ከሕዝብ ተለይቶ ፈጽሞ ይጠፋል።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያን ነቢይ የማትሰማው ነፍስም ሁሉ ከወገኖችዋ ተለይታ ትጥፋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያንም ነቢይ የማትሰማው ነፍስ ሁሉ ከሕዝብ ተለይታ ትጠፋለች’ አለ። |
የሚናገረው እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ በምድር ላይ ሲያስረዳቸው እምቢ ያሉት ካላመለጡ፥ ከሰማይ የመጣው ሲያስጠነቅቀን ፈቀቅ የምንል እኛ እንዴት እናመልጣለን?
እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበርና፥ የሰሙትም ለእኛ ይህንኑ አረጋግጠውልናል።