ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ ጌታ ተራራ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን።” ሕግ ከጽዮን፤ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
ሐዋርያት ሥራ 10:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነገውም ወደ ቂሣርያ ገቡ፤ ቆርኔሌዎስም ዘመዶቹንና የቅርብ ወዳጆቹን በአንድነት ጠርቶ ይጠባበቃቸው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሚቀጥለው ቀን ቂሳርያ ገባ። ቆርኔሌዎስም ዘመዶቹንና የቅርብ ወዳጆቹን ሰብስቦ ይጠብቃቸው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሁለተኛውም ቀን ወደ ቂሳርያ ደረሱ፤ ቆርኔሌዎስም ዘመዶቹንና የቅርብ ወዳጆቹን ጠርቶ እነጴጥሮስን ይጠባበቅ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በማግሥቱም ወደ ቂሳርያ ከተማ ገባ፤ ቆርኔሌዎስም ዘመዶቹንና የቅርብ ወዳጆቹን ጠርቶ ይጠብቃቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነገውም ወደ ቂሣርያ ገቡ፤ ቆርኔሌዎስም ዘመዶቹንና የቅርብ ወዳጆቹን በአንድነት ጠርቶ ይጠባበቃቸው ነበር። |
ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ ጌታ ተራራ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን።” ሕግ ከጽዮን፤ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፦ ኑ ወደ ጌታ ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ እኛም በፍለጋው እንሄዳለን ይላሉ፤ ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የጌታ ቃል ይወጣልና።