La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 2:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም አበኔር፥ “ወደ ቀኝህ ወይም ወደ ግራህ ዘወር በልና አንዱን ጎልማሳ ይዘህ ምርኮውን ውሰድ” አለው። አሣሄል ግን እርሱን ማሳደዱን ቀጠለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም አበኔር፣ “ወደ ቀኝህ ወይም ወደ ግራህ ዘወር በልና አንዱን ጕልማሳ ይዘህ መሣሪያውን ንጠቀው” አለው። አሣሄል ግን እርሱን መከታተሉን አልተወም ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አበኔርም “እኔን ማሳደድ ተው! ይልቅስ ከወታደሮቹ አንዱን በማሳደድ የያዘውን ምርኮ ውሰድ” አለው፤ ዐሣሄል ግን እርሱን ማሳደዱን ቀጠለ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አበ​ኔ​ርም፥ “ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ፈቀቅ በል፤ ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንድ ጐል​ማሳ ያዝ፤ መሣ​ሪ​ያ​ው​ንም ለራ​ስህ ውሰድ” አለው። አሣ​ሄል ግን እር​ሱን ከማ​ሳ​ደድ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አበኔርም፦ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ፈቀቅ በል፥ አንድ ጕልማሳ ያዝ፥ መሣርያውንም ውስድ አለው። አሣሄል ግን እርሱን ከማሳደድ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 2:21
3 Referencias Cruzadas  

አበኔርም ወደ ኋላው ዘወር ብሎ በመመልከት፥ “አሣሄል! አንተ ነህ?” ሲል፥ “አዎን እኔ ነኝ” ብሎ መለሰለት።


እንደገናም አበኔር፥ “እኔን ማሳደድህን ተው! እኔስ ስለምን ከመሬት ጋር ላጣብቅህ? ከዚያስ የወንድምህን የኢዮአብን ፊት እንዴት ብዬ አያለሁ?” አለው።


ከዚያም የጌታ መንፈስ በሳምሶን ላይ በኃይል ወረደበት፤ ወደ አስቀሎናም ወርዶ ከሰዎቻቸው መካከል ሠላሳውን ገደለ፤ ያላቸውንም ከገፈፈ በኋላ ልብሶቻቸውን አምጥቶ እንቈቅልሹን ለፈቱት ሰዎች ሰጣቸው። በቁጣ እንደነደደም ተነሥቶ ወደ አባቱ ቤት ወጣ።