መሳፍንት 14:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ከዚያም የጌታ መንፈስ በሳምሶን ላይ በኃይል ወረደበት፤ ወደ አስቀሎናም ወርዶ ከሰዎቻቸው መካከል ሠላሳውን ገደለ፤ ያላቸውንም ከገፈፈ በኋላ ልብሶቻቸውን አምጥቶ እንቈቅልሹን ለፈቱት ሰዎች ሰጣቸው። በቁጣ እንደነደደም ተነሥቶ ወደ አባቱ ቤት ወጣ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ከዚያም የእግዚአብሔር መንፈስ በሳምሶን ላይ በኀይል ወረደበት፤ ወደ አስቀሎናም ወርዶ ከሰዎቻቸው መካከል ሠላሳውን ገደለ፤ ያላቸውንም ከገፈፈ በኋላ ልብሶቻቸውን አምጥቶ እንቈቅልሹን ለፈቱት ሰዎች ሰጣቸው። በቍጣ እንደ ነደደም ተነሥቶ ወደ አባቱ ቤት ወጣ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 የእግዚአብሔርም መንፈስ ለእርሱ ብርታትን ሰጠው፤ ወደ አስቀሎናም ወርዶ ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፤ ውብ የሆነውንም ልብሳቸውን ሁሉ በመግፈፍ አምጥቶ የእንቆቅልሹን ፍች ላወቁት ሰዎች ሰጣቸው። በሆነውም ነገር ሁሉ እጅግ ተቈጥቶ ወደ ቤተሰቦቹ ተመለሰ፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ ወረደ፤ ወደ አስቀሎናም ወረደ፤ ከዚያም ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፤ ልብሳቸውንም ገፍፎ እንቆቅልሹን ለነገሩት ሰዎች ሰጠ። ሶምሶንም ተቈጣ፤ ወደ አባቱም ቤት ተመለሰ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ በኃይል ወረደ፥ ወደ አስቀሎናም ወረደ፥ ከዚያም ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፥ ልብሳቸውንም ወስዶ እንቈቅልሹን ለፈቱት ሰዎች ሰጠ። ቁጣውም ነደደ፥ ወደ አባቱም ቤት ወጣ። Ver Capítulo |