እነርሱም ጥቂት ሰዎችን መረጡ፤ ንጉሡም እነዚያን ሰዎች በሁለት ሠረገሎች እንዲቀመጡ አድርጎ በሶርያውያን ሠራዊት ላይ የደረሰውን ሁኔታ መርምረው እንዲመለሱ መመሪያ በመስጠት ላካቸው።
2 ነገሥት 7:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎቹም ከዚያ ተነሥተው እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ ዘልቀው ሄዱ፤ በየመንገዱም ሶርያውያን ሲሸሹ ጥለውት የሄዱትን ልብስና መሣሪያ ሁሉ አዩ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሰው መጥተው ይህን ሁሉ ለንጉሡ ነገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ተከተሏቸው። ሶርያውያን በጥድፊያ ሲሸሹ፣ የጣሉትንም ልብስና ዕቃ በየመንገዱ ላይ ተበታትኖ አገኙ፤ መልእክተኞቹም ተመልሰው ይህንኑ ለንጉሡ ነገሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎቹም ከዚያ ተነሥተው እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ ዘልቀው ሄዱ፤ በየመንገዱም ሶርያውያን ሲሸሹ ጥለውት የሄዱትን ልብስና መሣሪያ ሁሉ አዩ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሰው መጥተው ይህን ሁሉ ለንጉሡ ነገሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኋላቸውም እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ተከትለዋቸው ሄዱ፤ እነሆም፥ ሶርያውያን ሲሸሹ የጣሉት ልብስና ዕቃ መንገዱን ሁሉ ሞልቶ አገኙ። እነዚያ መልእክተኞችም ተመልሰው ለእስራኤል ንጉሥ ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኋላቸው እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ሄዱ፤ እነሆም፥ ሶርያውያን ሲሸሹ የጣሉት ልብስና ዕቃ መንገዱን ሁሉ ሞልቶ ነበር። መልእክተኞችም ተመልሰው ለንጉሡ ነገሩት። |
እነርሱም ጥቂት ሰዎችን መረጡ፤ ንጉሡም እነዚያን ሰዎች በሁለት ሠረገሎች እንዲቀመጡ አድርጎ በሶርያውያን ሠራዊት ላይ የደረሰውን ሁኔታ መርምረው እንዲመለሱ መመሪያ በመስጠት ላካቸው።
ሕዝቡም በፍጥነት እየተራወጠ ወጥቶ የሶርያን ሰፈር ዘረፈ፤ እግዚአብሔር አስቀድሞ በተናገረውም መሠረት ሦስት ኪሎ ምርጥ ስንዴ ወይም ስድስት ኪሎ ገብስ በአንድ ጥሬ ብር ተሸመተ።
በምትጎበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?
የአባቱንም ቤት ክብር ሁሉ ልጆቹንም የልጅ ልጆቹንም፥ እያንዳንዷን ትንንሽ ዕቃ፥ ከሲኒ ጀምሮ እስከ ጋን ድረስ ያለ የቤት ዕቃ ሁሉ በርሱ ላይ ይንጠለጠላል።
እንግዲህ እነደዚህ ዓይነት ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ማንኛውንም ሸክምና የተጣበቅንበትን ኅጢአት ሁሉ አራግፈን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት እንሩጥ።