2 ዜና መዋዕል 26:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሞናውያንም ለዖዝያን ገበሩ፤ እጅግም በርትቶ ነበርና ዝናው እስከ ግብጽ መግቢያ ድረስ ተሰማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሞናውያን ለዖዝያን ግብር ገበሩለት፤ ኀይሉ ስለ ገነነም ዝናው እስከ ግብጽ ዳርቻ ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐሞናውያንም ለዖዝያ ገበሩለት፤ እጅግ እየገነነ በመሄዱ ዝናው እስከ ግብጽ ድረስ ተሰማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሞናውያንም ለዖዝያን ገበሩ፤ እጅግም በርትቶ ነበርና ዝናው እስከ ግብፅ መግቢያ ድረስ ተሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሞናውያንም ለዖዝያን ገበሩ፤ እጅግም በርትቶ ነበርና ዝናው እስከ ግብፅ መግቢያ ድረስ ተሰማ። |
እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረገ፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፥ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር። ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት ተገዢዎች ሆኑ፤ ገበሩለትም።
እርሱ ከሰዎች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ጥበበኛ ነበረ። ከኤዝራሐዊው ኤታን፥ የማሖል ልጆች ከሆኑት ከሄማን፥ ከካልኮልና ከዳርዓዕ የሚበልጥ ጥበበኛ ነበረ፤ ዝናውም ከፍ ብሎ በጐረቤት ሕዝቦች ሁሉ ዘንድ አስተጋባ።
ከፍልስጥኤማውያንም ለኢዮሣፍጥ እጅ መንሻና የብር ግብር ያመጡ ነበሩ፤ ዓረባውያንም ደግሞ ከመንጎቻቸው ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ በጎችና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየሎች ያመጡለት ነበር።
ከአሞንም ልጆች ንጉሥ ጋር ተዋጋ አሸነፋአቸውም። በዚያም ዓመት የአሞን ልጆች መቶ መክሊት ብር፥ ዐሥር ሺህም የቆሬስ መስፈሪያ ስንዴ፥ ዐሥር ሺህም የቆሬስ መስፈሪያ ገብስ ሰጡት። እንዲሁም ደግሞ የአሞን ልጆች በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት ተመሳሳ መጠን ያለውን ግብር ገበሩለት።
ዝናው በመላዋ ሶርያ ሁሉ ተሰማ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይ ተይዘው የታመሙትን ሁሉ፥ አጋንንት ያደሩባቸውን፥ በጨረቃ የሚነሣባቸውንና ሽባዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
በአሞን ልጆች አቅራቢያ ስትደርስ፥ ለሎጥም ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከአሞን ልጆች ምድር ርስት አልሰጥህምና፥ አትጣላቸው አትውጋቸውም።’”
አሞናዊው ናዖስ ወጥቶ ያቢሽ ገለዓድን ከበባት፤ የያቢሽም ሰዎች ሁሉ ናዖስን፥ “ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፥ እኛም እንገዛልሃለን” አሉት።