ሰሎሞን ከኪራም መርከቦች ጋር በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ ሌሎች የተርሴስ መርከቦችም ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመት ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር።
2 ዜና መዋዕል 20:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮሣፍጥም ወደ ተርሴስ የሚሄዱትን መርከቦች ለመሥራት ከእርሱ ጋር ተባበረ፤ መርከቦቹንም በዔጽዩን-ጋብር አሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ተርሴስ የሚሄዱ መርከቦችን ለመሥራትም ተስማሙ፤ መርከቦቹንም በዔጽዮንጋብር አሠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱም በመተባበር ዔጽዮንጋብር ተብሎ በሚጠራ ወደብ ላይ ውቅያኖስን አቋርጠው ሊጓዙ የሚችሉ መርከቦችን ሠርተው ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ተርሴስም የሚሄዱትን መርከቦች ያሠራ ዘንድ ከእርሱ ጋር አንድ ሆነ፤ መርከቦቹንም በጋሲዮንጋብር አሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ተርሴስም የሚሄዱትን መርከቦች ያሠሩ ዘንድ አንድ ሆኑ፤ መርከቦቹንም በዔጽዩንጋብር አሠሩ። |
ሰሎሞን ከኪራም መርከቦች ጋር በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ ሌሎች የተርሴስ መርከቦችም ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመት ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር።
የመሪሳም ሰው የዶዳያ ልጅ አልዓዛር፦ “ከአካዝያስ ጋር ተባብረሃልና ጌታ ሥራህን አፍርሶታል” ብሎ በኢዮሣፍጥ ላይ ትንቢት ተናገረ። መርከቦቹም ተሰበሩ፥ ወደ ተርሴስም ለመሄድ አልቻሉም።
ለንጉሡም ከኪራም ባርያዎች ጋር ወደ ተርሴስ የሚሄዱ መርከቦች ነበሩት፤ በሦስት በሦስት ዓመትም አንድ ጊዜ የተርሴስ መርከቦች ወርቅና ብር የዝሆንም ጥርስ ዝንጀሮና ዝጉርጉር ወፍም ይዘው ይመጡ ነበር።