2 ዜና መዋዕል 12:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ሮብዓም በእርሱ ፋንታ የናስ ጋሻዎችን ሠራ፥ የንጉሡንም ቤት ደጅ በሚጠብቁ በዘበኞች አለቆች እጅ አኖራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ንጉሥ ሮብዓም እነዚህን ለመተካት ሲል፣ የናስ ጋሻዎች ሠርቶ የቤተ መንግሥቱን ቅጥር በር ለሚጠብቁ የዘብ አለቆች በኀላፊነት ሰጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሮብዓም ሺሻቅ በወሰዳቸው ጋሻዎች ምትክ፥ ሌሎች ጋሻዎችን ከነሐስ አሠርቶ፥ የቤተ መንግሥቱን ቅጽር በሮች በሚጠብቁ የዘበኞች አለቆች ኀላፊነት እንዲቀመጡ አደረገ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ሮብዓም በእነርሱ ፋንታ የናስ አላባሽ አግሬ ጋሻዎችን ሠራ፤ ሮብዓምም የንጉሡን ቤት ደጅ በሚጠብቁ በዘበኞች አለቃ እጅ አኖራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ሮብዓም በእርሱ ፋንታ የናስ ጋሻዎችን ሠራ፤ የንጉሡንም ቤት ደጅ በሚጠብቁ በዘበኞች አለቃ እጅ አኖራቸው። |
እነርሱንም ለመተካት ንጉሥ ሮብዓም ጋሻዎችን ከነሐስ አሠርቶ የቤተ መንግሥቱን ቅጽር በር የመጠበቅ ኀላፊነት ባላቸው የዘብ አለቆች እንዲጠበቁ አደረገ።
የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ የጌታንም ቤት መዛግብትና የንጉሡን ቤት መዛግብት ወሰደ፤ ሁሉንም ነገር ወሰደ፤ ደግሞም ሰሎሞን የሠራቸውን የወርቁን ጋሻዎች ወሰደ።