La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 11:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከእርሷም በኋላ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን አገባ፤ እርሷም አብያን፥ ዓታይን፥ ዚዛን፥ ሰሎሚትን ወለደችለት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን አገባ፤ እርሷም አብያ፣ ዓታይ፣ ዚዛ፣ ሰሎሚት የተባሉትን ወለደችለት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቈየት ብሎም ሮብዓም፥ ማዕካ ተብላ የምትጠራውን የአቤሴሎምን ልጅ አግብቶ አቢያ፥ ዓታይ፥ ዚዛና ሼሎሚት ተብለው የሚጠሩ አራት ወንዶች ልጆችን ወለደ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከእ​ር​ስ​ዋም በኋላ የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምን ልጅ መዓ​ካን አገባ፤ እር​ስ​ዋም አብ​ያን፥ ኢያ​ቲን፥ ዚዛን፥ ሰሎ​ሚ​ትን ወለ​ደ​ች​ለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከእርስዋም በኋላ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን አገባ፤ እርስዋም አብያን፥ ዓታይን፥ ዚዛንና ሰሎሚትን ወለደችለት።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 11:20
7 Referencias Cruzadas  

እርሷም የዑስ፥ ሰማራያ፥ ዘሃም የሚባሉትን ወንዶች ልጆች ወለደችለት።


ሮብዓምም ከሚስቶቹና ከቁባቶቹ ሁሉ ይልቅ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን ወደደ፤ ዐሥራ ስምንትም ሚስቶችና ስልሳ ቁባቶች ነበሩት፥ ሀያ ስምንት ወንዶችና ስልሳ ሴቶች ልጆች ወለደ።


ሮብዓምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም አብያ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።


ንጉሡም ኢዮርብዓም በነገሠ በዓሥራ ስምንተኛው ዓመት አብያ በይሁዳ ላይ ንጉሥ ሆነ።


ሦስት ዓመት በኢየሩሳሌም ነገሠ፤ የእናቱም ስም ሚካያ ነበረ፥ የገብዓ ሰው የኡርኤል ልጅ ነበረች። በአብያና በኢዮርብዓም መካከል ጦርነት ነበረ።


ሰሎሞን ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓም አቢያን ወለደ፤ አቢያም አሣፍን ወለደ፤