በሰሎሞን ላይ ያመፀው ሌላው ሰው በኤፍሬም ጸሬዳ ተብላ የምትጠራው ክፍለ ሀገር ተወላጅ የሆነ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ነው፤ እርሱም ከሰሎሞን አገልጋዮች አንዱ ነበር፤ እናቱም ጽሩዓ ተብላ የምትጠራ ባሏ የሞተባት ሴት ነበረች።
2 ዜና መዋዕል 10:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓምም ከንጉሡ ከሰሎሞን ፊት ሸሽቶ በግብጽ ይኖር ነበርና ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮርብዓም ከግብጽ ተመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከንጉሥ ሰሎሞን ሸሽቶ በግብጽ ይኖር የነበረው የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ይህን ሲሰማ፣ ከግብጽ ተመልሶ መጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከንጉሥ ሰሎሞን በመሸሽ ወደ ግብጽ ኮብልሎ የነበረው የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ይህን ወሬ በሰማ ጊዜ ከግብጽ ተመልሶ ወደ አገሩ ወደ እስራኤል መጣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓምም ከንጉሡ ከሰሎሞን ፊት ሸሽቶ በግብፅ ይኖር ነበርና ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮርብዓም ከግብፅ ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓምም ከንጉሡ ከሰሎሞን ፊት ሸሽቶ በግብጽ ይኖር ነበርና ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮርብዓም ከግብጽ ተመለሰ። |
በሰሎሞን ላይ ያመፀው ሌላው ሰው በኤፍሬም ጸሬዳ ተብላ የምትጠራው ክፍለ ሀገር ተወላጅ የሆነ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ነው፤ እርሱም ከሰሎሞን አገልጋዮች አንዱ ነበር፤ እናቱም ጽሩዓ ተብላ የምትጠራ ባሏ የሞተባት ሴት ነበረች።
ኢዮርብዓም ከፍ ያለ የሥራ ችሎታ ያለው ወጣት ነበር፤ ሰሎሞንም ይህ ወጣት ትጉህና ብርቱ ሠራተኛ መሆኑን በተመለከተ ጊዜ በምናሴና በኤፍሬም ነገዶች ግዛት ውስጥ ባሉት ገባሮች ሁሉ ላይ ኀላፊ አድርጎ ሾመው።
ከዚህም የተነሣ ሰሎሞን ኢዮርብዓምን ለመግደል ሞከረ፤ ነገር ግን ኢዮርብዓም ወደ ግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በመኰብለል አመለጠ፤ ሰሎሞንም እስከሞተበት ጊዜ ድረስ እዚያው ቆየ።
የቀረውም ፊተኛውና ኋለኛው የሰሎሞን ተግባራት በነቢዩ በናታን ታሪክ፥ በሴሎናዊውም በአሒያ ትንቢት፥ ስለ ናባጥም ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው በባለ ራእዩ በአዶ ራእይ በቃላት የተጻፈ አይደለምን?