1 ጢሞቴዎስ 5:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም በመጀመሪያ የገቡትን ቃል በማፍረሳቸው ምክንያት በራሳቸው ላይ ፍርድን ያመጣሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህም ፍርድን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ፤ በመጀመሪያ የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ሴቶች በመጀመሪያ ለክርስቶስ የገቡትን ቃል በማፍረሳቸውም በራሳቸው ላይ ፍርድን ያመጣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፊተኛውንም እምነታቸውን ስለ ናቁ ይፈረድባቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፊተኛውንም እምነታቸውን ስለ ናቁ ይፈረድባቸዋል፤ |
ከዚህም ጎን ለጎን ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ ፈቶችም ብቻ ሳይሆኑ የማይገባቸውን እየተናገሩ ሰውን የሚያሙና በነገር ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ።
ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአል፤ በቅድሚያም በእኛ የሚጀመር ከሆነ፥ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?