Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ጢሞቴዎስ 5:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እነዚህ ሴቶች በመጀመሪያ ለክርስቶስ የገቡትን ቃል በማፍረሳቸውም በራሳቸው ላይ ፍርድን ያመጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በዚህም ፍርድን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ፤ በመጀመሪያ የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በዚህም በመጀመሪያ የገቡትን ቃል በማፍረሳቸው ምክንያት በራሳቸው ላይ ፍርድን ያመጣሉ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የፊተኛውንም እምነታቸውን ስለ ናቁ ይፈረድባቸዋል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የፊተኛውንም እምነታቸውን ስለ ናቁ ይፈረድባቸዋል፤

Ver Capítulo Copiar




1 ጢሞቴዎስ 5:12
8 Referencias Cruzadas  

ወንድሞቼ ሆይ! እኛ አስተማሪዎች የሆንን የባሰ ፍርድ እንደምንቀበል ታውቃላችሁና ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አይሁኑ።


በክርስቶስ ጸጋ ከጠራችሁ አምላክ እንዲህ ፈጥናችሁ መለየታችሁና ወደ ሌላ ወንጌል ማዘንበላችሁ ያስደንቀኛል።


ፍርድ የሚጀመርበት ጊዜ ቀርቦአል፤ ፍርዱ የሚጀመረውም በእግዚአብሔር ሰዎች ላይ ነው፤ ታዲያ፥ ፍርድ የሚጀመረው በእኛ ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ ሰዎች መጨረሻቸው ምን ይሆን?


መሰብሰባችሁ ለፍርድ እንዳይሆን ከመካከላችሁ የራበው ሰው ቢኖር በቤቱ ይብላ። ስለ ቀረው ነገር እኔ እዚያ ስመጣ ተጨማሪ መመሪያ እሰጣችኋለሁ።


ባሎቻቸው የሞቱባቸው በዕድሜ ያልገፉ ሴቶች ሥጋዊ ምኞታቸው አሸንፎአቸው ለክርስቶስ ያላቸው ፍቅር ሲቀነስ ባል ማግባት ስለሚፈልጉ እነርሱን በመበለቶች መዝገብ አትጻፋቸው።


ደግሞም ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ መፍታት ብቻ ሳይሆን በየሰዉ ቤት እየዞሩ ሰውን የሚያሙ፥ በሰው ነገር የሚገቡና መናገር የማይገባቸውን የሚናገሩ ይሆናሉ።


ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ በጎ ነገርን ስለ ጠሉ ጠላት ያሳድዳቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios