1 ጢሞቴዎስ 4:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህን ነገሮች እዘዝ፤ አስተምርም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህን ነገሮች እዘዝ፤ አስተምርም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህን ነገሮች እዘዝ፤ አስተምርም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህን እዘዝና አስተምር። በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን እዘዝና አስተምር። በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው። |
የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለ ሆኑ አይናቋቸው፤ ይልቁንስ ከበፊት ይልቅ ያገልግሏቸው ምክንያቱም በመልካም ሥራቸው የሚጠቀሙት አማኞችና ወዳጆቻቸው ናቸውና። እነዚህን ነገርች አስተምርና ምከር።
ቃሉ የታመነ ነው። እግዚአብሔርንም የሚያምኑት በመልካም ሥራ በጥንቃቄ እንዲተጉ፥ እነዚህን አስረግጠህ እንድትናገር እፈቅዳለሁ። ይህ መልካምና ለሰዎች የሚጠቅም ነው፤