La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 25:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አቢግያም ወዲያውኑ በአህያ ላይ ተቀምጣ አምስት አገልጋዮቿን በማስከተል፥ ከዳዊት መልእክተኞች ጋር ሄደች፤ ለዳዊትም ሚስት ሆነችው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አቢግያም ወዲያውኑ በአህያ ላይ ተቀምጣ ዐምስት አገልጋዮቿን በማስከተል፣ ከዳዊት መልእክተኞች ጋራ ሄደች፤ ለዳዊትም ሚስት ሆነችው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፈጥናም ተነሥታ በአህያዋ ላይ ተቀመጠች፤ በአምስት ገረዶችዋም ታጅባ ከዳዊት አገልጋዮች ጋር በመሄድ ሚስቱ ሆነች።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤ​ግ​ያም ፈጥና ተነ​ሣች፤ በአ​ህ​ያም ላይ ተቀ​መ​ጠች፤ አም​ስ​ቱም ገረ​ዶ​ችዋ ተከ​ተ​ሉ​አት፤ የዳ​ዊ​ት​ንም መል​እ​ክ​ተ​ኞች ተከ​ትላ ሄደች፤ ሚስ​ትም ሆነ​ችው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አቢግያም ፈጥና ተነሣች፥ በአህያም ላይ ተቀመጠች፥ አምስቱም ገረዶችዋ ተከተሉአት፥ የዳዊትንም መልእክተኞች ተከትላ ሄደች፥ ሚስትም ሆነችው።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 25:42
7 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ዳዊት ወደዚያ ወጣ፤ ሁለቱ ሚስቶቹ ኢይዝራኤላዊቷ አሒኖዓምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢጌልም ከእርሱ ጋር ነበሩ።


ዳዊት በኬብሮን እያለ፥ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ የበኲር ልጁ፥ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአሒኖዓም የተወለደው አምኖን፥


ሁለተኛው፥ የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢጌል የተወለደው ኪልአብ፥ ሦስተኛው፥ ተልማይ ከተባለው ከገሹር ንጉሥ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፥


ዳዊትና ሰዎቹ በጋት በአኪሽ ዘንድ ተቀመጡ፤ እያንዳንዱ ሰው ከቤተሰቡ ጋር ነበረ፤ ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ጋር፥ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአሒኖዓም እና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ አቢጌል ጋር ነበር።


ሁለቱ የዳዊት ሚስቶች ማለትም ኢይዝራኤላዊቷ አሒኖዓምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢጌልም ተማርከው ነበር።