1 ሳሙኤል 24:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያደረግህልኝን በጎ ነገር ይኸው ነግረኸኛል፤ ጌታ እኔን በእጅህ ቢጥልልህም አንተ ግን አልገደልኸኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሆኑ ጠላቱን አግኝቶ ጕዳት ሳያደርስበት የሚለቀው ማን ነው? ዛሬ ስላደረግህልኝ ቸርነት እግዚአብሔር ይመልስልህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላት በእጁ ገብቶለት ጒዳት ሳያደርስበት የሚለቀው ሰው ከቶ የት ይገኛል? ዛሬ ለእኔ ስላደረግኸው መልካም ነገር እግዚአብሔር ይባርክህ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ዛሬ በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶኝ ሳለ አልገደልኸኝምና ለእኔ መልካም እንዳደረግኽልኝ ለእኔ ነገርኸኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠላቱን አግኝቶ በመልካም መንገድ ሸኝቶ የሚሰድድ ማን ነው? ስለዚህ ለእኔ ስላደረግኸው ቸርነት እግዚአብሔር ይመልስልህ። |
እናቱን፥ “አንድ ሺህ አንድ መቶ ሰቅል ብር ተሰርቆብሽ፥ የሰረቀውን ሰው ስትራገሚ ሰምቼሽ ነበር፤ ብሩ ከእኔ ዘንድ ይገኛል፤ የወሰድሁት እኔ ነኝ” አላት። ከዚያም እናቱ፥ “ልጄ፤ ጌታ ይባርክህ” አለችው።
እርሱም፥ “አትፍራ፤ አባቴ ሳኦል እጁን በአንተ ላይ አያሳርፍም፤ በእስራኤል ላይ ትነግሣለህ፤ እኔም ካንተ ቀጥዬ ሁለተኛ ሰው እሆናለሁ፤ ይህንም አባቴ ሳኦል እንኳ ያውቀዋል” አለው።
ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ጽድቁና እንደ ታማኝነቱ ይክፈለው። እኔ ግን ዛሬ አንተን ጌታ በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኝ ሳለ ጌታ በቀባው ላይ እጄን አላነሣሁም።
ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ፤ የተባረክህ ሁን፤ ብዙ ነገር ታደርጋለህ፤ በእርግጥም ይከናወንልሃል” አለው። ስለዚህም ዳዊት ወደሚሄድበት ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ስፍራው ተመለሰ።