በል እንግዲህ ሕዝቦች ሁሉና በኢየሩሳሌም የቀሩ ሰዎች እንዳደረጉት አንተ በመጀመሪያ ቅደምና በንጉሡ የተወሰነውን ነገር ፈጽም፤ አንተና ልጆችህ ቁጥራችሁ ከንጉሡ ወዳጆች ጋር ይሆናል፤ ብርና ወርቅ ይሰጣችሁና ብዙ ስጦታዎችም ይደረግላችሁና ትከብራላችሁ”።