1 ቆሮንቶስ 13:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍቅር ሁሉን ይታገሣል፤ ሁሉን ያምናል፤ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፤ በሁሉ ነገር ይጸናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍቅር ሁልጊዜ ይታገሣል፤ ሁልጊዜ ያምናል፤ ሁልጊዜ ተስፋ ያደርጋል፤ ሁልጊዜ ጸንቶ ይቆማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍቅር ያለው ሰው ሁሉን ይችላል፤ በሁሉም ላይ እምነቱን ይጥላል፤ በሁሉም ላይ ተስፋ ያደርጋል፤ በሁሉ ነገር ይጸናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሁሉ ያቻችላል፤ በሁሉም ያስተማምናል፤ በሁሉም ተስፋ ያስደርጋል፥ በሁሉም ያስታግሣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል። |
ሌሎች በእናንተ ላይ ይህን የመካፈል መብት ያላቸው ከሆነ፥ እኛማ ይልቁን አይኖረንም? በዚህ መብት ግን አልተጠቀምንም፥ ነገር ግን የክርስቶስን ወንጌል በምንም እንዳንከለክል በሁሉ እንታገሣለን እንጂ።
ስለዚህ በምትታገሱት መከራችሁና በስደታችሁ ሁሉ ስለ እናንተ መጽናትና እምነት እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት በእናንተ እንመካለን።
ስደቴንም፥ መከራዬንም ተከተልህ፤ በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የደረሰብኝን ነገርና የታገሥሁትን ስደት ታውቃለህ፤ ጌታ ግን ከሁሉም አዳነኝ።