1 ቆሮንቶስ 1:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው መመዘኛ ብዙዎች ጥበበኞች አልነበሩም፥ ብዙዎች ኀያላን አልነበሩም፥ ብዙዎች ታላላቅ ሰዎች አልነበሩም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞች ሆይ፤ በተጠራችሁ ጊዜ ምን እንደ ነበራችሁ እስኪ አስቡ። በሰው መስፈርት ከእናንተ ብዙዎቻችሁ ዐዋቂዎች አልነበራችሁም፤ ብዙዎቻችሁም ኀያላን አልነበራችሁም፤ ብዙዎቻችሁም ከትልቅ ቤተ ሰብ አልተወለዳችሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔር በጠራችሁ ጊዜ ምን ዐይነት ሰዎች እንደ ነበራችሁ አስታውሱ፤ እንደ ሰው አስተሳሰብ ከእናንተ መካከል ብዙዎች ጥበበኞች ወይም ብርቱዎች ወይም ታላላቅ ሰዎች አልነበሩም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቻችን! እንግዲህ እንዴት እንደ ተጠራችሁ እዩ፤ በሥጋ እጅግ ብዙዎች ዐዋቂዎች አይደላችሁምና፥ ብዙዎች ኀያላንም አይደላችሁምና፥ በዘመድም ብዙዎች ደጋጎች አይደላችሁምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም። |
በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሴት አድርጎ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ! ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጽክላቸው አመሰግንሃለሁ፤ አዎን አባት ሆይ! መልካም ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።
እርሱም አስተዋይ ሰው ከሆነው ሰርግዮስ ጳውሎስ ከሚባለው አገረ ገዥ ጋር ነበረ። ይህም በርናባስንና ሳውልን ወደ እርሱ ጠርቶ የእግዚአብሔርን ቃል ሊሰማ ፈለገ።
አንዳንዶች ወንዶች ግን ተባብረው አመኑ፤ ከእነርሱ ደግሞ በአርዮስፋጎስ ያለው የፍርድ ቤት ፈራጅ ዲዮናስዮስ ደማሪስ የሚሉአትም አንዲት ሴት ሌሎችም ከእነርሱ ጋር ነበሩ።
ይህን ደግሞ፥ መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን፥ መንፈስ በሚያስተምረን ቃል እንናገራለን እንጂ ከሰው ጥበብ በሚገኝ ቃል አይደለም።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለጸጋ እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱም ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?