ነገር ግን የአብርሃም ለነበሩትም ለቁባቶቹ ልጆች አብርሃም ስጦታ ሰጣቸው፥ እርሱም ገና በሕይወቱ ሳለ ከልጁ ከይስሐቅ ለይቶ ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ አገር ሰደዳቸው።
1 ዜና መዋዕል 8:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሸሐራይምም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን እንዲሄዱ ካሰናበተ በኋላ በሞዓብ ሜዳ ልጆች ወለደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሸሐራይም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከፈታ በኋላ በሞዓብ ምድር ወንዶች ልጆች ወለደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሻሐራም፥ ሑሺምና ባዕራ ተብለው የሚጠሩትን ሁለት ሚስቶቹን ፈታ፤ ዘግየት ብሎም በሞአብ አገር ሲኖር ሖዴሽ ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት አግብቶ ሰባት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ዮባብ፥ ጺብያ፥ ሜሻ፥ ማልካም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሐራይምም ሚስቶቹን ሑሴምንና በዕራን ከሰደደ በኋላ በሞዓብ ሜዳ ልጆችን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሸሐራይምም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከሰደደ በኋላ በሞዓብ ሜዳ ልጆች ወለደ። |
ነገር ግን የአብርሃም ለነበሩትም ለቁባቶቹ ልጆች አብርሃም ስጦታ ሰጣቸው፥ እርሱም ገና በሕይወቱ ሳለ ከልጁ ከይስሐቅ ለይቶ ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ አገር ሰደዳቸው።
መሳፍንት ይፈርዱ በነበረበት ዘመን በአገሩ ላይ ረሀብ ሆነ። አንድ ሰውም ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር በሞዓብ ምድር ለመቀመጥ ከቤተልሔም ይሁዳ ተነሥቶ ሄደ።