1 ዜና መዋዕል 3:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሐናንያም ልጆች ፈላጥያና የሻያ ነበሩ። የረፋያ ልጆች፥ የአርናን ልጆች፥ የአብድዩ ልጆች፥ የሴኬንያ ልጆች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሐናንያ ዘሮች፤ ፈላጥያ፣ የሻያ፤ እንዲሁም የረፋያ፣ የአርናን፣ የአብድዩና የሴኬንያ ወንዶች ልጆች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐናንያም ፈላጥያና ይሻዕያ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ይሻዕያም ረፋያን ወለደ፤ ረፋያም አርናንን ወለደ፤ አርናን አብድዩን ወለደ፤ አብድዩም ሸካንያን ወለደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሐናንያም ልጆች ፈላጥያና ልጁ ኢያሴያ ነበሩ። ረፋያ ልጁ፥ አርና ልጁ፥ አብድዩ ልጁ፥ ሴኬንያ ልጁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሐናንያም ልጆች ፈላጥያና የሻያ ነበሩ። የረፋያ ልጆች፥ የአርናን ልጆች፥ የአብድዩ ልጆች፥ የሴኬንያ ልጆች። |
በካህናቱም ከተሞች ለታላላቆችና ለታናናሾች ወንድሞቻቸው በየሰሞናቸው ድርሻቸውን በታማኝነት እንዲሰጡ ዔድን፥ ሚንያሚን፥ ኢያሱ፥ ሸማያ፥ አማርያ፥ ሴኬንያ የቆሬ ረዳቶች ነበሩ።