ስለዚህ ዳዊት የጌታን ታቦት አብሮት እንዲሆን ወደ ዳዊት ከተማ ይዞት ለመሄድ አልፈለገም፤ በዚህ ፈንታ አቅጣጫ ለውጦ የጌት ሰው ወደ ሆነው ወደ ዖቤድ ኤዶም ቤት ወሰደው።
1 ዜና መዋዕል 26:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ልጆቻቸውም ወንድሞቻቸውም ለማገልገል ኃያላን የነበሩ የዖቤድ-ኤዶም ልጆች ስልሳ ሁለት ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ሁሉ የዖቤድኤዶም ዘሮች ሲሆኑ፣ እነርሱም ሆኑ ወንዶች ልጆቻቸውና ቤተ ዘመዶቻቸው ሥራውን ለመሥራት በቂ ችሎታ ነበራቸው። የዖቤድኤዶም ዘሮች በአጠቃላይ ስድሳ ሁለት ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ሁሉ የዖቤድኤዶም ልጆች ነበሩ፦ እነርሱና ልጆቻቸው እንዲሁም ዘመዶቻቸው የሥራ ችሎታና ሥራውን የመሥራት ጥንካሬ ነበራቸው፤ የዖቤድኤዶም ልጆችና የልጅ ልጆች በጠቅላላው ሥልሳ ሁለት ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ ሁሉ የዖቤድኤዶም ልጆች ነበሩ፤ እነርሱም፥ ልጆቻቸውም፥ ወንድሞቻቸውም ለማገልገል ኀያላን የነበሩ የዖቤድኤዶም ልጆች ስድሳ ሁለት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ ሁሉ የዖቤድኤዶም ልጆች ነበሩ፤ እነርሱም ልጆቻቸውም ወንድሞቻቸውም ለማገልገል ኃያላን የነበሩ የዖቤድኤዶም ልጆች ስድሳ ሁለት ነበሩ። |
ስለዚህ ዳዊት የጌታን ታቦት አብሮት እንዲሆን ወደ ዳዊት ከተማ ይዞት ለመሄድ አልፈለገም፤ በዚህ ፈንታ አቅጣጫ ለውጦ የጌት ሰው ወደ ሆነው ወደ ዖቤድ ኤዶም ቤት ወሰደው።
የሸማያ ልጆች፤ ዖትኒ፥ ራፋኤል፥ ዖቤድ፥ ኤልዛባድ ነበሩ፤ ኤልዛባድም ኃያላን ወንድሞች የነበሩት እነርሱም ኤሊሁና ሰማክያ ነበሩ። እነዚህ ሁሉ የዖቤድ-ኤዶም ልጆች ነበሩ፤
እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ላልሆነ፥ ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንድንሆን አበቃን፤ ፊደል ይገድላል፤ መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።
ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠው ኃይል ያገልግል፤ በዚህም ዓይነት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብራል፤ ክብርና ሥልጣን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።