ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጥበብ 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 የቀና ነገርን ሳያስቡ ራሳቸው እንዲህ አሉ፥ ሕይወታችን ጥቂት ነው፥ የሚያሳዝንም ነው-። ለሰውም ሞት መድኀኒት የለውም፥ ከመቃብርም የተመለሰ የታወቀ የለምና። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 የሚያቀርቡት የተሳሳተ ክርክርም ይህ ነው፥ ለራሳቸውም እንዲህ ይላሉ፦ ሕይወታችን አጭርና አሳዛኝ ናት፤ ፍጻሜያችን በደረሰ ጊዜ መዳኛ የለንም፤ ከሙታን ሀገር የተመለሰ ሰው አናውቅም። ምዕራፉን ተመልከት |