ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ሲራክ 38:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 በወናፍ አጠገብ የሚቀመጥ፥ የብረትንም ሥራ የሚማር አንጥረኛ እንደ እርሱ ነው። የወናፉም ጢስ ሰውነቱን ያሻክረዋል። እሳቱም ሰውነቱን ያቀልጣታል፤ የመዶሻውም ድምፅ ጆሮውን ያደነቍረዋል። ዐይኖቹም ወደ መሣሪያው ይመለከታሉ፤ በልቡም ሥራውን ይጨርስ ዘንድ ያስባል፤ ትጋቱም መሣሪያውንና ወናፉን ያሳምር ዘንድ ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 ከመስፉ አጠገብ የሚቀመጠውም አንጥረኛ እንዲሁ ነው። ከብረቱ ምን እንደሚቀርጽ ያስባል፥ የእሳቱ ወላፈን ቆዳውን ይለበልበዋል፥ ከወናፉ ሙቀትም ጋር ይታገላል፥ የመዶሻው ድምፅ ያደነቁረዋል፥ ዐይኖቹም በሚያወጣቸው ቅርጾች ላይ ተተክለዋል፥ ቀልቡን በሥራው ላይ ያሳርፋል፥ ሥራውንም በሚገባ ካላጠናቀቀ ቢመሽ እንኳ አያርፍም። ምዕራፉን ተመልከት |