ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ሲራክ 38:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 ሌሊቱ ቀን የሚሆንባቸው ጠራቢና የጠራቢዎች አለቃ፥ የማኅተም ቅርጽ የሚቀርጹና የሚያለዝቡ ሰዎች እንደ እርሱ ናቸው፤ እነዚህም አሳባቸው ሁሉ በየመልኩ መስለው ይሠሩ ዘንድ ነው፤ ምክራቸውም ሁሉ ማኅተሙን ማለዘብን ይጠነቀቁ ዘንድ ነው፤ ትጋታቸውም ሥራቸውን ይፈጽሙ ዘንድ ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 ሠራተኞችና የእጅ ባለሙያዎችም፥ ቀን ከሌት ይደክማሉና እንዲሁ ናቸው። ማኀተሞች የሚቀርጹ፥ አዳዲስ ንድፋቸውንም መልሰው የሚቀርጹ፥ ሥራቸውንም ለማጠናቀቅ ሌትም የሚሠሩ፤ ባተሌዎች በመሆናቸው ጥበብን ለመቅሰም ጊዜ አይኖራቸውም። ምዕራፉን ተመልከት |