Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤፌሶን 4:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ተስፋ የቈ​ረጡ ናቸው፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ለጕ​ስ​ቍ​ልና፥ ለር​ኵ​ሰ​ትና ለመ​ዳ​ራት አሳ​ል​ፈው ሰጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ኅሊናቸው ስለ ደነዘዘ በማይረካ ምኞት፣ በርኩሰት ሁሉ እንዳሻቸው ለመኖር ቅጥ ለሌለው ብልግና ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ኅሊናቸው ስለ ደነዘዘ፥ በማይረካ ምኞት ርኩሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ለሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የዕፍረት ስሜታቸው ስለ ጠፋ ርኲሰቶችን ሁሉ ለመፈጸም ራሳቸውን ለሥጋዊ ምኞታቸው አሳልፈው ሰጥተዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ደንዝዘውም በመመኘት ርኵሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤፌሶን 4:19
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይል​ቁ​ንስ አስ​ጸ​ያ​ፊና የረ​ከሰ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም እንደ ውኃ የሚ​ጠጣ ሰው ምንኛ ያንስ?


ሁሉም ከቶ የማ​ይ​ጠ​ግቡ የረ​ከሱ ውሾች ናቸው፤ እነ​ር​ሱም ያስ​ተ​ውሉ ዘንድ የማ​ይ​ችሉ ክፉ​ዎች ናቸው፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው እንደ ፈቃ​ዳ​ቸው መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለ​ዋል።


ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና፤


እን​ግ​ዲህ በል​ባ​ቸው ከንቱ አሳብ እን​ደ​ሚ​ኖሩ እንደ አሕ​ዛብ እን​ዳ​ት​ኖሩ ይህን እላ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እመ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ።


ምድ​ራዊ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም ከዝ​ሙ​ትና ከር​ኵ​ሰት፥ ከጥ​ፋ​ትና ከክፉ ምኞት፥ ጣዖት ማም​ለክ ከሆ​ነው ከቅ​ሚ​ያም ግደ​ሉት።


የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።


“ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፤” ደግሞ “የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች፤” እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል።


ወዮላቸው! በቃየል መንገድ ሄደዋልና፤ ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል፤ በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።


አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቍጣ ወይን ጠጅ የተነሣ ወድቀዋልና፤ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ፤ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኀይል የተነሣ ባለጠጋዎች ሆኑ፤” ብሎ ጮኸ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች