ኤፌሶን 4:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ልቡናቸው የተጨፈነ ነው፤ በስንፍናቸውና በድንቍርናቸው እግዚአብሔር ከሚሰጣቸው ሕይወት የተለዩ ናቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 እነርሱ ከልባቸው መደንደን የተነሣ ስለማያስተውሉ ልቡናቸው ጨልሟል፤ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ተለይተዋል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 እነርሱ ባለማወቃቸውና በልባቸው ደንዳንነት ምክንያት፥ ልቡናቸው ጨለመ፤ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ራቁ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 የእነርሱ አእምሮ ጨልሞአል፤ ባለማወቃቸውና በእልኸኛነታቸው ምክንያት እግዚአብሔር ከሚሰጠው ሕይወት ተለይተዋል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 እነርሱ ባለማወቃቸው ጠንቅ በልባቸውም ደንዳንነት ጠንቅ ልቡናቸው ጨለመ፥ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ራቁ፤ ምዕራፉን ተመልከት |