Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 7:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ኢያሱ የዘንበሪን ቤተ ሰብ አባላት አንድ በአንድ ወደ ፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከዚያም ከይሁዳ ነገድ የሆነውም የዛራ ልጅ፣ የዘንበሪ ልጅ፣ የከርሚ ልጅ አካን ለብቻው ተለየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የቤቱንም ሰዎች አንድ በአንድ አቀረበ፤ ከይሁዳም ነገድ የሆነ የዛራ ልጅ የዘንበሪ ልጅ የከርሚ ልጅ አካን ተለየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የዛብዲንም ቤተሰብ በየግለሰቡ ለይቶ አቀረበ፤ በመጨረሻም የዛብዲ የልጅ ልጅ የሆነው የካርሚ ልጅ ዓካን ለብቻው ተለየ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በዘ​ን​በ​ሪም ወገን ምል​ክት ታየ፤ የዘ​ን​በ​ሪም ቤተ ሰብ እያ​ን​ዳ​ንዱ ተለየ፤ ከይ​ሁ​ዳም ወገን በሆነ በከ​ርሚ ልጅ በዘ​ን​በሪ ልጅ በዛራ ልጅ በአ​ካን ላይ ምል​ክት ታየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ዘንበሪም ተለየ፥ የቤቱንም ሰዎች አቀረበ፥ ከይሁዳም ነገድ የሆነ የከርሚ ልጅ የዘንበሪ ልጅ የዛራ ልጅ አካን ተለየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 7:18
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መጥፎ ዕድል ኀጢአተኛን ይከታተላል፤ ብልጽግና ግን የጻድቃን ዋጋ ነው።


“ሌባ በተያዘ ጊዜ እንደሚያፍር፣ የእስራኤልም ቤት ዐፍሯል፤ እነርሱ፣ ንጉሦቻቸውና ሹሞቻቸው፣ ካህናታቸውና ነቢያታቸው እንዲሁ ያፍራሉ።


“ይህን ባታደርጉ ግን እግዚአብሔርን ትበድላላችሁ፤ ኀጢአታችሁ እንደሚያገኛችሁም ዕወቁ።


የይሁዳንም ጐሣዎች ወደ ፊት አቀረበ፤ ከእነዚህም የዛራን ጐሣ ለየ፤ እነዚህን ደግሞ በየቤተ ሰባቸው እንዲወጡ አደረገ፤ ከእነዚህም ዘንበሪ ተለየ።


ሳኦልም፣ “በእኔና በልጄ በዮናታን መካከልም ዕጣ ጣሉ” አላቸው። ዕጣውም በዮናታን ላይ ወደቀ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች