Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 7:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በዘ​ን​በ​ሪም ወገን ምል​ክት ታየ፤ የዘ​ን​በ​ሪም ቤተ ሰብ እያ​ን​ዳ​ንዱ ተለየ፤ ከይ​ሁ​ዳም ወገን በሆነ በከ​ርሚ ልጅ በዘ​ን​በሪ ልጅ በዛራ ልጅ በአ​ካን ላይ ምል​ክት ታየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ኢያሱ የዘንበሪን ቤተ ሰብ አባላት አንድ በአንድ ወደ ፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከዚያም ከይሁዳ ነገድ የሆነውም የዛራ ልጅ፣ የዘንበሪ ልጅ፣ የከርሚ ልጅ አካን ለብቻው ተለየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የቤቱንም ሰዎች አንድ በአንድ አቀረበ፤ ከይሁዳም ነገድ የሆነ የዛራ ልጅ የዘንበሪ ልጅ የከርሚ ልጅ አካን ተለየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የዛብዲንም ቤተሰብ በየግለሰቡ ለይቶ አቀረበ፤ በመጨረሻም የዛብዲ የልጅ ልጅ የሆነው የካርሚ ልጅ ዓካን ለብቻው ተለየ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ዘንበሪም ተለየ፥ የቤቱንም ሰዎች አቀረበ፥ ከይሁዳም ነገድ የሆነ የከርሚ ልጅ የዘንበሪ ልጅ የዛራ ልጅ አካን ተለየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 7:18
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በደለኞችን ክፉ ነገር ይከተላቸዋል፤ ጻድቃንን ግን መልካም ነገር ያገኛቸዋል።


ሌባ በተ​ያዘ ጊዜ እን​ደ​ሚ​ያ​ፍር፤ እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ እነ​ር​ሱና ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ውም፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ያፍ​ራሉ።


እን​ዲህ ባታ​ደ​ርጉ ግን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ፤ ክፉ ነገር ባገ​ኛ​ችሁ ጊዜ በደ​ላ​ች​ሁን ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


የይ​ሁ​ዳም ወገ​ኖች ተለዩ፤ በዛ​ራም ወገን ምል​ክት ታየ፤ የዛ​ራም ወገን በየ​ቤተ ሰቡ ተለየ፤


ሳኦ​ልም፥ “በእ​ኔና በዮ​ና​ታን መካ​ከል ዕጣ አጣ​ጥ​ሉን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕጣ ያወ​ጣ​በ​ትም ይሞ​ታል” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሳኦ​ልን፥ “እን​ዲህ ያለ ነገር አይ​ሆ​ንም” አሉት፤ ሳኦ​ልም ሕዝ​ቡን እንቢ አላ​ቸው። በእ​ር​ሱና በልጁ በዮ​ና​ታን መካ​ከ​ልም ዕጣ አጣ​ጣሉ። ዕጣ​ውም በልጁ በዮ​ና​ታን ላይ ወጣ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች