Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 13:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 እርሱ ይህን ተናግሮ እንዳበቃ የዳዊት ልጆች ገብተው መላቀስ ጀመሩ፤ ዳዊትና መኳንንቱም በመረረ ሁኔታ አለቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ገና ተናግሮ ሳይጨርስ፣ የንጉሡ ልጆች ጮኸው እየተላቀሱ ገቡ፤ እንደዚሁም ንጉሡና አገልጋዮቹ ሁሉ እጅግ አለቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 እርሱም ተናግሮ እንዳበቃ፥ የንጉሡ ልጆች ጮኸው እየተላቀሱ ገቡ፤ እንደዚሁም ንጉሡና አገልጋዮቹ ሁሉ አምርረው አለቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ተና​ግ​ሮም በጨ​ረሰ ጊዜ እነሆ፥ ወዲ​ያው የን​ጉሥ ልጆች ገቡ፤ ድም​ፃ​ቸ​ው​ንም ከፍ አድ​ር​ገው አለ​ቀሱ፤ ደግ​ሞም ንጉ​ሡና ብላ​ቴ​ኖቹ ሁሉ እጅግ ታላቅ ልቅሶ አለ​ቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ተናግሮም በጨረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ ወዲያው የንጉሥ ልጆች ገቡ፥ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ፥ ደግሞ ንጉሡና ባሪያዎቹ ሁሉ እጅግ ታላቅ ልቅሶ አለቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 13:36
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ባለሟሎቹም “ይህ ነገር ምን እንደ ሆነ ለማወቅ አልቻልንም፤ ሕፃኑ በሕይወት በነበረበት ጊዜ በመጾም አለቀስክለት፤ እርሱ ከሞተ በኋላ ግን ወዲያውኑ ተነሥተህ ተመገብክ!” አሉት።


ከዚያም በኋላ አምኖን እጅግ አድርጎ ጠላት፤ እንዲያውም ቀድሞ ካፈቀራት ይበልጥ አሁን በእርስዋ ላይ ያለው ጥላቻ ስለ ባሰ “ከዚህ ውጪልኝ!” አላት።


ዮናዳብም ዳዊትን “ልክ እኔ አገልጋይህ እንዳልኩት እነሆ፥ የንጉሡ ልጆች መጥተዋል፤” አለው።


አቤሴሎምም ሸሽቶ የገሹር ንጉሥ ወደ ሆነው ወደ ዓሚሁድ ልጅ ወደ ታልማይ ሄደ፤ በዚያም ሦስት ዓመት ቈየ፤ ዳዊት ስለ ልጁ ስለ አምኖን ሞት ለረዥም ጊዜ በማዘን አለቀሰ፤


ንጉሡም እጅግ አዘነ፤ በቅጽር በሩ አናት ላይ ወደሚገኘውም ክፍል ወጥቶ አለቀሰ፤ ወደዚያም ሲመጣ “ልጄ ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! አቤሴሎም ልጄ! ምነው በአንተ ምትክ እኔ በሞትኩ ልጄ ሆይ! አቤሴሎም ልጄ!” እያለ በመጮኽ ያለቅስ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች