2 ሳሙኤል 13:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም37-38 አቤሴሎምም ሸሽቶ የገሹር ንጉሥ ወደ ሆነው ወደ ዓሚሁድ ልጅ ወደ ታልማይ ሄደ፤ በዚያም ሦስት ዓመት ቈየ፤ ዳዊት ስለ ልጁ ስለ አምኖን ሞት ለረዥም ጊዜ በማዘን አለቀሰ፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም37 አቤሴሎም ኰብልሎ የጌሹር ንጉሥ ወደ ሆነው ወደ ዓሚሁድ ልጅ ወደ ተልማይ ሄደ፤ ነገር ግን ዳዊት ስለ ሞተው ልጁ ዘወትር ያለቅስ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)37 አቤሴሎም ግን ኰብልሎ የገሹር ንጉሥ ወደ ሆነው ወደ ዓሚሁድ ልጅ ወደ ታልማይ ሄደ፤ ዳዊትም ዘወትር ስለ ልጁ ያለቅስ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)37 አቤሴሎም ግን ኰብልሎ ወደ መአክ ሀገር ወደ ጌድሶር ንጉሥ ወደ አሚሁድ ልጅ ወደ ቶልማይዮ ሄደ። ዳዊትም ሁል ጊዜ ለልጁ ያለቅስ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)37 አቤሴሎም ግን ኮብልሎ ወደ ጌሹር ንጉሥ ወደ ዓሚሁድ ልጅ ወደ ተልማይ ሄደ። ዳዊትም ሁልጊዜ ለልጁ ያለቅስ ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |