Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 13:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ተና​ግ​ሮም በጨ​ረሰ ጊዜ እነሆ፥ ወዲ​ያው የን​ጉሥ ልጆች ገቡ፤ ድም​ፃ​ቸ​ው​ንም ከፍ አድ​ር​ገው አለ​ቀሱ፤ ደግ​ሞም ንጉ​ሡና ብላ​ቴ​ኖቹ ሁሉ እጅግ ታላቅ ልቅሶ አለ​ቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ገና ተናግሮ ሳይጨርስ፣ የንጉሡ ልጆች ጮኸው እየተላቀሱ ገቡ፤ እንደዚሁም ንጉሡና አገልጋዮቹ ሁሉ እጅግ አለቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 እርሱም ተናግሮ እንዳበቃ፥ የንጉሡ ልጆች ጮኸው እየተላቀሱ ገቡ፤ እንደዚሁም ንጉሡና አገልጋዮቹ ሁሉ አምርረው አለቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 እርሱ ይህን ተናግሮ እንዳበቃ የዳዊት ልጆች ገብተው መላቀስ ጀመሩ፤ ዳዊትና መኳንንቱም በመረረ ሁኔታ አለቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ተናግሮም በጨረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ ወዲያው የንጉሥ ልጆች ገቡ፥ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ፥ ደግሞ ንጉሡና ባሪያዎቹ ሁሉ እጅግ ታላቅ ልቅሶ አለቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 13:36
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ብላ​ቴ​ኖ​ቹም፥ “ይህ ስለ ሕፃኑ ያደ​ረ​ግ​ኸው ነገር ምን​ድን ነው? እርሱ በሕ​ይ​ወት ሳለ ጾም​ህና አለ​ቀ​ስህ፤ እን​ቅ​ል​ፍም አጣህ፤ ሕፃኑ ከሞተ በኋላ ግን ተነ​ሥ​ተህ እን​ጀራ በላህ፤ ጠጣ​ህም” አሉት።


ከዚ​ያም በኋላ አም​ኖን ፈጽሞ ጠላት፤ አስ​ቀ​ድሞ ከአ​ፈ​ቀ​ራት ፍቅር ይልቅ በኋላ የጠ​ላት ጥል በለጠ። አም​ኖ​ንም፥ “ተነ​ሥ​ተሽ ሂጂ” አላት።


ኢዮ​ና​ዳ​ብም ንጉ​ሡን፥ “እነሆ፥ የን​ጉሡ ልጆች መጥ​ተ​ዋል፤ አገ​ል​ጋ​ይህ እን​ዳ​ለው እን​ዲሁ ሆኖ​አል” አለው።


አቤ​ሴ​ሎም ግን ኰብ​ልሎ ወደ መአክ ሀገር ወደ ጌድ​ሶር ንጉሥ ወደ አሚ​ሁድ ልጅ ወደ ቶል​ማ​ይዮ ሄደ። ዳዊ​ትም ሁል ጊዜ ለልጁ ያለ​ቅስ ነበር።


ንጉ​ሡም እጅግ ደነ​ገጠ፤ በበ​ሩም ላይ ወዳ​ለ​ችው ሰገ​ነት ወጥቶ አለ​ቀሰ፤ ሲሄ​ድም፥ “ልጄ አቤ​ሴ​ሎም ሆይ፥ ልጄ፥ ልጄ አቤ​ሴ​ሎም ሆይ፥ በአ​ንተ ፋንታ እኔ እን​ድ​ሞት ቤዛ​ህም እን​ድ​ሆን ማን ባደ​ረ​ገኝ፥ ልጄ አቤ​ሴ​ሎም፥ ልጄ ሆይ፥” ይል ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች