ዘፀአት 40:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውን በመገናኛው ድንኳን በማደሪያው መግቢያ ፊት አኖረ፥ የሚቃጠልና የእህልን መሥዋዕት ሠዋበት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውንም በማደሪያው፣ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ አኖረው፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን መሥዋዕት በላዩ ላይ አቀረበ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 እዚያም በድንኳኑ መግቢያ ፊት ለፊት የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን መሠዊያ አኖረ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቊርባን እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በእርሱ ላይ አቀረበ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያም በምስክሩ ድንኳን ደጅ አኖረ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው በላዩ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን አቀረበ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያ በመገናኛው ድንኳን በማደሪያው ደጅ ፊት አኖረ፥ የሚቃጠለውንና የእህልን መሥዋዕት ሠዋበት። ምዕራፉን ተመልከት |