ሴቶች1 በምትወዳት ሚስትህ ላይ አትቅና፤ እንዴት እንደምትጎዳህ አታስተምራት፤ 2 እራስህን በሴት እጅ አትጣል። ካልሆነ ግን በቁጥጥር ሥር ትወድቃለህ። 3 ከሴተኛ አዳሪ ጋር አተዋዋል፥ በወጥመዷ ልትወድቅ ትችላለህና። 4 አንተ በተንኮል ሥራዋ እንዳትጠመድ፥ አዝማሪት ሴትን አታዘውትር። 5 ውብ ኮረዳን አትመልከት፤ ምናልባት አንተ እና እርሷ አንድ ዓይነት ቅጣት በራሳችሁ ላይ ታመጡ ይሆናል። 6 ለጋለሞታዎች ልብህን አትስጥ፤ ካልሆነ ግን ርስትህን ታጣለህ። 7 በከተማ መንገዶች ዙሪያ፥ ዐይኖችህ አያማትሩ። ጭር ወዳለው ቦታም አትሂድ። 8 ከቆንጆ ሴት ዓይንህን መልስ፤ የሌላ የሆነውን ውበት አትከጅል። በሴት ቁንጅና ምክንያት ብዙዎች ተሳስተዋል፤ ይህም ስሜትን እንደ እሳት ያቀጣጥላል። 9 ባል ካላት ሴት ዓይንህን መልስ፤ ከሷ ጋር አብረህ ወይን ጠጅ አትጠጣ፤ ልብህም ወደ እርሷ ከተሳበ፥ ራስህን መግታት አቅቶህ ችግር ላይ ትወድቃለህ። ከሰዎች ጋርስ ለሚኖርህ ግንኙነት10 የቀድሞ ወዳጅህን አትተው፤ አዲስ ወዳጅህ እሱን አይተካከለውም፤ አዲስ ወዳጅ እንደ አዲስ ወይን ጠጅ ነው፤ ሲያረጅ ደስ እያለህ ትጠጣዋለህ። 11 በኃጢአተኛ መልካም ዕድል አትቅና፤ ምን ዓይነት አሳዛኝ ፍጻሜ እንደሚጠብቀው አታውቅምና። 12 ክፉዎችን ደስ የሚያሰኛቸው አንተን አያስደስትህም፤ ከመሞታቸው በፊተ በዚህ ዓለም ሳይቀጡ እንደማይቀሩ አስታውስ። 13 ለመግደል ችሎታ ካለው ሰው ራቅ፤ የሞት ፍርሃት አያድርብህም። ግን ወደሱ ስትቀርብ በጣም ተጠንቀቅ፤ ሊገድልህ ይችላል፤ በወጥመድ መካከል የምትሄድና በከተማይቱ ምሽግ ላይ የምትራመድ መሆንህን አትዘንጋ። 14 በተቻለህ መጠን ጓደኛህን አትተው፤ ከጥበበኞች ጋር ተማከር። 15 ዕውቀት ካላቸው ሰዎች ጋር ተነጋገር፤ ንግግሮችህ ሁሉ ስለ ልዑል እግዚአብሔር ሕግ ይሁን። 16 ጻድቃኖች ካንተ ጋር የሚመግገቡ ጓደኞችህ ይሁኑ፤ ኩራትህ እግዚአብሔርን በመፍራት ይሁን። 17 ብልሃተኛ በእጁ ሥራ ይመሰገናል፥ የሕዝብ አለቃ በቃሉ ጥበብ ይመሰገናል፤ 18 ለፋላፊ ሰው ለከተማው ሽብር ነው። ልቅ ተናጋሪም አይወደድም። |