Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽሐፈ ሲራክ 10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


መስተዳድር

1 ጥበበኛ ገዢ ሕዝቡን ያስተምራል፤ ተከታዮንም ሥርዓት ያስተምራል።

2 ዳኛው እንደ ሆነው ባለሥልጣናቱም ይሆናሉ፤ የከተማው ገዢ እንደ ሆነው ነዋሪዎቹም ይሆናሉ።

3 አላዋቂ ንጉሥ የሕዝቡ ጥፋት ነው፤ የአንዲት ከተማ ብልጽግና በመሪዎቿ አስተዋይነት ይወሰናል።

4 የምድር አስተዳደር በእግዚአብሔር እጅ ነው፥ በትክክለኛው ወቅት ሁነኛ መሪ ያስነሣላታል።

5 የሰው ሥራ መቃናት በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ክብሩን የሚያሳርፈው የሕግ መምህር በሆነው ሰው ላይ ነው።

6 በባልንጀራህ ላይ በምንም ዓይነት በበደሉ ቂም አትያዝበት፥ በቁጣ ተነሣሥተህ ምንም ነገር አታድርግ። በበደሉ ቂም አትያዝበት፤ በቁጣ ተነሣሥተህ ምንም ነገር አታድርግ።

7 ትዕቢት በእግዚአብሔርም ሆነ በሰው ዘንድ የተጠላ ነው፤ ፍትሕን ማጓደል በሁለቱም ዘንድ የተወገዘ ነው።

8 ፍትሕን በማዛባት በንዋይ የተነሣ ነጻነት፥ ከአንድ ሕዝብ ወደ ሌላ ሕዝብ ይዛወራል።

9 አፈርና አመድ የሆነ ሰው ስለምን ይታበያል? እሱ ገና በሕይወቱ ሳለ የሆድ ዕቃው የበሰበሰ ነው።

10 የቆየ በሽታ ሐኪሙን ያቄላል፤ የዛሬ ንጉሥ የነገ አስክሬን ነው።

11 በሞትም ጊዜ ከፊሉ ሥጋችን ነፍሳት፥ አራዊትና ትሎች ይሆናሉ።

12 የትዕቢት መነሻው እግዚአብሔርን መክዳት፥ ልቦናንም ከፈጣሪ ማራቅ ነው።

13 የትዕቢት መጀመሪያው ኃጢአት በመሆኑ፥ በሱ የሚጸና አሰቃቂ ጥፋት ይመጣበታል፥ እግዚአብሔርም በነኝህ ሰዎች ላይ ያልታሰበ ቅጣትን ያወርዳል፥ ያጠፋቸውማል።

14 እግዚአብሐር ኃያላንን፥ ልዑላንን ከዙፋናቸው ገርስሷል፤ በምትካቸውም ትሑታንን አስቀምጧል።

15 እግዚአብሐር ትዕቢተኞችን ከሥራቸው መነገለ፤ በነሱ ቦታ የበታቾቹን ተከለ።

16 እግዚአብሔር የሕዝቦችን ምድር ገለባበጠ፥ እስከ መሠረታቸው ደመሰሳቸው፤

17 ከሰዎች መካከል አውጥቶ ጣላቸው፥ አጠፋቸው፥ መታሰቢያቸውንም ፋቀ፥፥

18 ትዕቢት ለሰው ልጆች፥ ቁጣም ከሴት ለተወለዱ አልተፈጠረም፤


ክብር የሚገባቸው ሰዎች

19 የትኛው ዘር ነው ክብር የሚገባው? ክብር የሚገባው የሰው ዘር ነው። ክብር የሚገባው የትኛው ዘር ነው? ክብር የሚገባው እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነው። መወገዝ የሚገባው የትኛው ዘር ነው? የሰው ዘር ነው። መወገዝ የሚገባው ዘር የትኛው ነው? የእግዚአብሔርን ሕግ የሚያፈርሰው ነው።

20 ሹም በወንድሞቹ መካከል ይከበራል፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩ በእግዚአብሔር ዘንድ ይከበራሉ።

22 ባለጸጎች፥ ታላላቅ ሰዎች፥ ድሆች፤ እግዚአብሔርን በመፍራታቸው ሊመካ ይገባል።

23 ዕውቀት ያለውን ድሃ መስደብ ደግ አይደለም፤ ኃጢአተኛን ማክበር የተገባ አይደለም።

24 ባለጸጎች፥ ዳኞች፥ ገዢዎች ሁሉ ክብር ይገባቸዋል፤ እግዚአብሔርን ከሚፈራ የበለጠ ታላቅ ሰው ግን የለም።

25 ብልህ አገልጋይ የሚያገለግሉትን ነጻ ሰዎች ይኖሩታል፤ አዋቂም ሰው ቅር አይሰኝም።


ግልጽነትና ትሕትና

26 ሥራህን በምትሠራበት ጊዜ ብዙም አትራቀቅ፤ በመከራ ጊዜ እንዲሁ አትኰፈስ፤

27 ጠንክሮ በመሥራት ፍላጎቱን ማሟላት የቻለ፤ ላንዴ እንኳን የሚበላው ከሌለው ትምክህተኛ ይሻላል።

28 ልጄ ሆይ በራስህ አትመጻደቅ፥ ስለ ራስህም ተገቢው ግምት ይኑርህ።

29 እራሱን የሚጎዳውን ማን ይቀበለዋል? እራሱንስ የሚጠላውን ማን ያከብረዋል?

30 ደሃ በዕውቀቱ፥ ሀብታም በሀብቱ ይከበራል።

31 በድህነቱ የከበረ በጸጋ ቢሆንማ ኖሮ፤ ምን ያህል በላቀ፤ በሀብቱ ያልተከበረ ቢደኸይማ ምን ይሆን ነበር፤

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች