ጦብያንም አለው፥ “ትሄዱ ዘንድ፥ ትከናወኑም ዘንድ ተዘጋጁ።” ልጁም ለመንገድ ስንቃቸውን አዘጋጀ፤ አባቱም አለው፥ “ከዚህ ሰው ጋር ሂድ፤ በሰማያት የሚኖር እግዚአብሔር መንገዳችሁን ያቅናላችሁ፤ መልአኩም አብሮአችሁ ይሂድ፤” ሁለቱም ወጥተው ሄዱ፤ ሌላው ልጃቸውም ተከተላቸው።
ከደሞዝህ ሌላም እጨምርልሃለሁ።” መልአኩም “ከእርሱ ጋር እሄዳለሁ፥ አትፍራ፤ በደኀና ሄደን በደኀና እንመለሳለን፤ መንገዱ አያሰጋም” አለው።