“ልጄ ሆይ! አሁንም ከነነዌ ውጣ፤ ነቢዩ ዮናስ የተናገረው ነገር በግድ ይደረጋልና።
አሁንም ልጆቼ ሆይ ይህን ግዴታ እጥልባችሁአለሁ፤ ከልባችሁ እግዚአብሔርን አገልግሉ፤ እርሱን ደስ የሚያሰኘውን ነገር አድርጉ፤ ልጆቻችሁም ጽድቅን እንዲያደርጉ፥ ምጽዋትን እንዲያሰጡ፥ እግዚአብሔርን እንዲያስታውሱና ስሙን ሁልጊዜ ከልባቸውና በሙሉ ኃይላቸው እንዲባርኩ ግዴታ ጣሉባቸው።