በጎዳናዋ ሁሉ ሃሌ ሉያ ይላሉ፤ እያመሰገኑም እንዲህ ይላሉ፥ “እግዚአብሔር ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይመስገን።”
የኢየሩሳሌም በሮች የምስጋና መዝሙርን ያስተጋባሉ፥ ቤቶችም በሙሉ “ሃሌ ሉያ! የእስራኤል አምላክ ይባረክ” ይላሉ። በውስጥሽም ቅዱሱን ስም፥ ለዘለዓለም ዓለም ይባርካሉ።