እነሆም፥ ልጄ ጦብያን አየሁት፤” ከዚህም በኋላ ልጁ ደስ እያለው ገባ፤ ለአባቱም በሜዶን የተደረገለትን ታላላቅ ነገር ሁሉ ነገረው።
አለቀሰ። “የዓይኔ ብርሃን ልጄ አየሁህ” አለ። ቀጥሎም እንዲህ አለ “እግዚአብሔር ይባረክ፤ ታላቅ ስሙ ይባረክ፤ ቅዱሳን መላእክት ሁሉ ይባረኩ፤ ታላቅ ስሙ ለዘለዓለም የተባረከ ይሁን፤ መላእክት ሁሉ ለዘለዓለም የተመሰገኑ ይሁኑ፤