ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 11:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ጦቢትም ደስ እያለው ወጥቶ ምራቱን ተቀበላት፤ እግዚአብሔርንም በነነዌ አደባባይ አመሰገነው፤ ሲሄድም ያዩት ሰዎች፥ “እንዴት አየ?” ብለው አደነቁት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 በመከራ ቀጥቶኝ ነበር፥ ምሕረት አደርገልኝ፥ አሁን ልጄን ጦብያን አየሁት።” ጦብያ ደስ ብሎት በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ቤት ገባ። ሁሉንም ነገር ማለትም መንገዱ እንዴት እንደ ተቃናለት፥ ገንዘቡንም ተቀብሎ እንደመጣ፥ የራጉኤልን ልጅ ሣራን እንዴት እንደአገባት በነነዌ ከተማ አጠገብ እንደደረሰችና በቅርብ እንደምትምጣ ለአባቱ ተረከለት። ምዕራፉን ተመልከት |