ሁለቱ ልጆቹ እስኪገድሉት ድረስ፥ ሸሽተውም ወደ አራራት ተራራ እስኪሄዱ ድረስ አምሳ አምስት ቀን ከቤቴ አልወጣሁም። ልጁ አስራዶንም በእርሱ ፋንታ ነገሠ፤ የወንድሜ ልጅ የአናሔል ልጅ አኪአኪሮስንም በአባቱ ቤት ሁሉና በሥራታቸው ሁሉ ላይ ሾመው።
ይህ ከሆነ አርባ ቀን ሳይሞላው ሁለቱ ልጆቹ ንጉሡን ገደሉት፥ ከዛም ወደ አራራት ተራራዎች ሸሹ፤ ልጁ ኤሳራዶን ተተካ። የወንድሜ የአናኤል ልጅ አሂካር የመንግሥት ገንዘብ አስተዳዳሪና የአስተዳደሩ ዋና ሆኖ ተሾመ።