ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 1:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 አኪአኪሮስም ማለደልኝ፤ ወደ ነነዌም መለሰኝ። አኪአኪሮስም የማኅተምና የቤቱ ንብረት ጠባቂ ነበር። አስራዶንም ዳግመኛ ሾመው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ከዚህ በኋላ አሂካር አማለደኝና ወደ ነነዌ እንድመለስ ተፈቀደልኝ። በአሦር ንጉሥ በሰናክሬም ጊዜ አሂካር የወይን ጠጅ ቀጂዎች አለቃ፥ የመንግሥት ማኀተም ጠባቂ፥ የገንዘብ ቤቱ አስተዳዳሪና ነበር። ንጉሡ ኤሳራዶንም በዚህ በሥራው ላይ በድጋሚ ሾመው። እርሱም ዘመዴ የወንድሜ ልጅ ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |