የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 12:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የረ​ዳ​ኝን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ፤ ለል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስምም እዘ​ም​ራ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእግዚአብሔር ቃል የጠራ ቃል ነው፤ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ፣ በምድር ላይ በከውር እንደ ተፈተነ ብር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለ ምስኪኖች መከራ፥ ስለ ችግረኞች ጩኸት ጌታ፦ አሁን እነሣለሁ ይላል፥ የተጠሙትንም ደኅንነት አመጣላቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች የታመኑ ናቸው፤ በእሳት ምድጃ ሰባት ጊዜ እንደ ነጠረ ብር የጠሩ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 12:6
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የኀ​ያል አም​ላክ መን​ገድ ንጹሕ ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ጽኑዕ ነው፤ በእ​ሳ​ትም የጋለ ነው፤ በእ​ር​ሱም ለሚ​ታ​መ​ኑት ጠባ​ቂ​ያ​ቸው ነው።


የደ​ካ​ሞ​ችን ቤቶች አፍ​ር​ሶ​አ​ልና፤ ያል​ሠ​ራ​ው​ንም ቤት በዝ​ብ​ዞ​አ​ልና።


“በእ​ው​ነቱ ብር የሚ​ወ​ጣ​በት ቦታ አለ፥ ወር​ቅም የሚ​ነ​ጠ​ር​በት ስፍራ አለ።


እነ​ርሱ ተሰ​ነ​ካ​ክ​ለው ወደቁ፤ እኛ ግን ተነ​ሣን፥ ጸን​ተ​ንም ቆምን።


እነሆ፥ ዛሬ ጀመ​ርሁ አልሁ፥ ልዑል ቀኙን እን​ደ​ሚ​ያ​ፈ​ራ​ርቅ።


አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ ጠላ​ቶቼም የሚ​ያ​መ​ጡ​ብ​ኝን መከራ እይ፥ ከሞት ደጆች ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ር​ገኝ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “በግ​ብፅ ያለ​ውን የሕ​ዝ​ቤን መከራ በእ​ው​ነት አየሁ፦ ከአ​ሠ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰማሁ፤ ሥቃ​ያ​ቸ​ው​ንም ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤


ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም እጅ አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ ከዚ​ያ​ችም ሀገር ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ሀገር፥ ወደ ሰፊ​ዪ​ቱና ወደ መል​ካ​ሚቱ ሀገር፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ስፍራ አወ​ጣ​ቸው ዘንድ ወረ​ድሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “በጸ​ናች እጅ ይለ​ቅ​ቃ​ቸ​ዋ​ልና፥ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ ከም​ድሩ አስ​ወ​ጥቶ ይሰ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ልና አሁን በፈ​ር​ዖን የማ​ደ​ር​ገ​ውን ታያ​ለህ።”


እግዚአብሔር ፍርዱን ይፈርድለታልና። አንተም ነፍስህን በሰላም ታድናለህ።


“በእ​ነ​ርሱ ላይ እነ​ሣ​ለሁ” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ስም​ንና ቅሬ​ታን፥ ዘር​ንና ትው​ል​ድ​ንም አጠ​ፋ​ለሁ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “አሁን እነ​ሣ​ለሁ፤ አሁን እከ​ብ​ራ​ለሁ፤ አሁን ከፍ ከፍ እላ​ለሁ።