መዝሙር 12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒምመዝሙር 12 ለመዘምራን አለቃ፤ በሸሚኒት የሚዘመር፤ የዳዊት መዝሙር። 1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ደግ ሰው የለምና አንተው ድረስልኝ! ከሰዎችም መካከል አንድ ታማኝ አይገኝም። 2 እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤ በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራሉ። 3 ሸንጋዩን ከንፈር ሁሉ፣ ነገር የምታበዛውንም ምላስ እግዚአብሔር ያጥፋ! 4 እነዚህም፣ “በአንደበታችን እንረታለን፤ ከንፈራችን የእኛ ነው፤ ጌታችንስ ማነው?” የሚሉ ናቸው። 5 እግዚአብሔር፣ “ስለ ችግረኞች መከራ፣ ስለ ድኾችም ጩኸት፣ አሁን እነሣለሁ፤ በናፈቁትም ሰላም አኖራቸዋለሁ” ይላል። 6 የእግዚአብሔር ቃል የጠራ ቃል ነው፤ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ፣ በምድር ላይ በከውር እንደ ተፈተነ ብር ነው። 7 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ትጠብቀናለህ፤ ከዚህም ትውልድ ለዘላለም ትከልለናለህ። 8 በሰዎች ዘንድ ክፋት ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ፣ ዐመፀኞች በየአቅጣጫው በዛቻ ይዞራሉ። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
Biblica, Inc.