የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 7:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ ድን​ኳ​ኑን ፈጽሞ በተ​ከ​ለ​ባት፥ እር​ስ​ዋ​ንና ዕቃ​ዋን ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት፥ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንና ዕቃ​ው​ንም ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት ቀን፥

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሙሴ የማደሪያ ድንኳኑን ተክሎ ካበቃ በኋላ ማደሪያ ድንኳኑንና ዕቃዎቹን ሁሉ ቀባቸው፤ ቀደሳቸውም፤ እንደዚሁም መሠዊያውንና ዕቃዎቹን በሙሉ ቀባቸው፤ ቀደሳቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ማደሪያውን ተክሎ ከጨረሰ በኋላ፥ እርሱንና ዕቃውን ሁሉ ከቀባና ከቀደሰ በኋላ፥ መሠዊያውንና ዕቃውንም ሁሉ ከቀባና ከቀደሰ በኋላ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሙሴ የመገናኛውን ድንኳን ተክሎ በፈጸመበት ቀን ድንኳኑንና የመገልገያ ዕቃዎቹን፥ መሠዊያውንና የመገልገያ ዕቃዎቹን፥ ዘይት በመቀባት ቀደሳቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ማደሪያውን ፈጽሞ ከተከለ በኋላ፥ እርሱንና ዕቃውን ሁሉ ከቀባና ከቀደሰ በኋላ፥ መሠዊያውንና ዕቃውንም ሁሉ ከቀባና ከቀደሰ በኋላ፤

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 7:1
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰባ​ተ​ኛ​ዋን ቀን ባረ​ካት፤ ቀደ​ሳ​ትም፤ ሊፈ​ጥ​ረው ከጀ​መ​ረው ሥራ ሁሉ በእ​ር​ስዋ ዐር​ፎ​አ​ልና።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያለው የናሱ መሠ​ዊያ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን የሰ​ላ​ሙ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ስብ ይይዝ ዘንድ ታናሽ ስለ ነበረ፥ በዚያ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የሰ​ላ​ሙ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ስብ አሳ​ር​ጎ​አ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት የነ​በ​ረ​ውን የአ​ደ​ባ​ባ​ዩን መካ​ከል ንጉሡ በዚያ ቀን ቀደሰ።


“በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ከሰ​ውም፥ ከእ​ን​ስ​ሳም መጀ​መ​ሪያ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ማሕ​ፀ​ንን የሚ​ከ​ፍት በኵር ሁሉ ለእኔ ለይ​ልኝ፤ የእኔ ነው።”


ዕለት ዕለ​ትም ስለ ማስ​ተ​ስ​ረይ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ኑን ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ ማስ​ተ​ስ​ረ​ያም ባደ​ረ​ግህ ጊዜ መሠ​ዊ​ያ​ውን ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ቅዱ​ስም ይሆን ዘንድ ትቀ​ባ​ዋ​ለህ።


የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ው​ንም ቀብ​ተህ ትቀ​ድ​ሳ​ለህ።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ንገ​ራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ከእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ከየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት አንድ አንድ በትር፥ ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም ከየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በት​ሮች ውሰድ፤ የእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱ​ንም ስም በየ​በ​ትሩ ላይ ጻፍ።


መሠ​ዊ​ያ​ውም በተ​ቀባ ቀን አለ​ቆቹ መሠ​ዊ​ያ​ውን ለመ​ቀ​ደስ ቍር​ባ​ንን አቀ​ረቡ፤ አለ​ቆ​ችም መባ​ቸ​ውን በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት አቀ​ረቡ።


መሠ​ዊ​ያው በተ​ቀባ ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ​ቆች ለመ​ሠ​ዊ​ያው መቀ​ደሻ ያቀ​ረ​ቡት መባ ይህ ነበረ፤ ዐሥራ ሁለት የብር ወጭ​ቶች፥ ዐሥራ ሁለት የብር ድስ​ቶች፥ ዐሥራ ሁለት የወ​ርቅ ጭል​ፋ​ዎች፤


የደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከብት ሁሉ፥ ሃያ አራት ጊደ​ሮች፥ ስድ​ሳም አውራ በጎች፥ ስድ​ሳም አውራ ፍየ​ሎች፥ ስድ​ሳም ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበሩ። መሠ​ዊ​ያው ከተ​ቀባ በኋላ ለመ​ቀ​ደ​ሻው የቀ​ረበ ቍር​ባን ይህ ነበረ።


እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች! ማናቸው ይበልጣል? መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው?