Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ዘኍል 7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆች መባእ

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ ድን​ኳ​ኑን ፈጽሞ በተ​ከ​ለ​ባት፥ እር​ስ​ዋ​ንና ዕቃ​ዋን ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት፥ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንና ዕቃ​ው​ንም ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት ቀን፥

2 ዐሥራ ሁለቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆች፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች፥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አቀ​ረቡ፤ እነ​ዚ​ህም ከተ​ቈ​ጠ​ሩት በላይ የተ​ሾሙ የነ​ገ​ዶች አለ​ቆች ነበሩ።

3 መባ​ቸ​ው​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረቡ፤ የተ​ከ​ደኑ ስድ​ስት ሰረ​ገ​ሎች ዐሥራ ሁለ​ትም በሬ​ዎች፤ በየ​ሁ​ለ​ቱም አለ​ቆች አንድ ሰረ​ገላ አቀ​ረቡ፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ አንድ በሬ በድ​ን​ኳኑ ፊት አቀ​ረቡ።

4 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦

5 “ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግል ይሆን ዘንድ፥ ከእ​ነ​ርሱ ተቀ​ብ​ለህ ለሌ​ዋ​ው​ያን ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ስጣ​ቸው።”

6 ሙሴም ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና በሬ​ዎ​ችን ተቀ​ብሎ ለሌ​ዋ​ው​ያን ሰጣ​ቸው።

7 ለጌ​ድ​ሶን ልጆች እንደ አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ሁለት ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና አራት በሬ​ዎ​ችን ሰጣ​ቸው።

8 ከካ​ህ​ኑም ከአ​ሮን ልጅ ከኢ​ታ​ምር እጅ በታች ላሉት ለሜ​ራሪ ልጆች እንደ አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው መጠን አራት ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ስም​ንት በሬ​ዎ​ችን ሰጣ​ቸው።

9 ለቀ​ዓት ልጆች ግን መቅ​ደ​ሱን ማገ​ል​ገል የእ​ነ​ርሱ ነውና፥ በት​ከ​ሻ​ቸ​ውም ይሸ​ከ​ሙት ነበ​ርና ምንም አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።

10 መሠ​ዊ​ያ​ውም በተ​ቀባ ቀን አለ​ቆቹ መሠ​ዊ​ያ​ውን ለመ​ቀ​ደስ ቍር​ባ​ንን አቀ​ረቡ፤ አለ​ቆ​ችም መባ​ቸ​ውን በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት አቀ​ረቡ።

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እያ​ን​ዳ​ንዱ አለቃ በየ​ቀኑ መሠ​ዊ​ያ​ውን ለመ​ቀ​ደስ እያ​ን​ዳ​ንዱ አለቃ መባ​ውን በቀን በቀኑ ያቅ​ርብ” አለው።

12 በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ቀን መባ​ውን ያቀ​ረበ ከይ​ሁዳ ነገድ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን ነበረ።

13 መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤

14 ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤

15 ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት ከመ​ን​ጋ​ዎች አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤

16 ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤

17 ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ የነ​አ​ሶን መባ ይህ ነበረ።

18 በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን የይ​ሳ​ኮር አለቃ የሰ​ገር ልጅ ናት​ና​ኤል አቀ​ረበ።

19 ለመ​ባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞ​ሉ​ትን፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆ​ነ​ውን አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆ​ነ​ውን አንድ የብር ድስት፤

20 ዕጣ​ንም የተ​ሞ​ላ​ውን ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆ​ነ​ውን አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤

21 ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤

22 ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤

23 ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች አቀ​ረበ፤ የሰ​ገር ልጅ የና​ት​ና​ኤል መባ ይህ ነበረ።

24 በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን የዛ​ብ​ሎን ልጆች አለቃ የኬ​ሎን ልጅ ኤል​ያብ መባ​ውን አቀ​ረበ።

25 መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤

26 ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤

27 ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤

28 ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤

29 ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የኬ​ሎን ልጅ የኤ​ል​ያብ መባ ይህ ነበረ።

30 በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ቀን የሮ​ቤል ልጆች አለቃ የሴ​ድ​ዮር ልጅ ኤሊ​ሱር መባ​ውን አቀ​ረበ፤

31 መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ስቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤

32 ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤

33 ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤

34 ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤

35 ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የሴ​ድ​ዮር ልጅ የኤ​ሊ​ሱር መባ ይህ ነበረ።

36 በአ​ም​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን የስ​ም​ዖን ልጆች አለቃ የሲ​ሩ​ሳዴ ልጅ ሰላ​ም​ያል መባ​ውን አቀ​ረበ፤

37 መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤

38 ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤

39 ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤

40 ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤

41 ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የሲ​ሩ​ሳዴ ልጅ የሰ​ላ​ም​ያል መባ ይህ ነበረ።

42 በስ​ድ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን የጋድ ልጆች አለቃ የራ​ጉ​ኤል ልጅ ኤሊ​ሳፍ መባ​ውን አቀ​ረበ፤

43 መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤

44 ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤

45 ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት ጠቦት፤

46 ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤

47 ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የራ​ጉ​ኤል ልጅ የኤ​ሊ​ሳፍ መባ ይህ ነበረ።

48 በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን የኤ​ፍ​ሬም ልጆች አለቃ የኤ​ሚ​ሁድ ልጅ ኤሊ​ሳማ መባ​ውን አቀ​ረበ፤

49 መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑ ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤

50 ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤

51 ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤

52 ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤

53 ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የኤ​ሚ​ሁድ ልጅ የኤ​ሊ​ሳማ መባ ይህ ነበረ።

54 በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን የም​ናሴ ልጆች አለቃ የፈ​ዳ​ሱር ልጅ ገማ​ል​ያል መባ​ውን አቀ​ረበ፤

55 መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑ ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤

56 ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤

57 ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤

58 ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤

59 ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የፈ​ዳ​ሱር ልጅ የገ​ማ​ል​ያል መባ ይህ ነበረ።

60 በዘ​ጠ​ነ​ኛ​ውም ቀን የብ​ን​ያም ልጆች አለቃ የጋ​ዴ​ዮን ልጅ አቢ​ዳን መባ​ውን አቀ​ረበ፤

61 መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤

62 ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤

63 ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤

64 ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤

65 ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የጋ​ዴ​ዮን ልጅ የአ​ቢ​ዳን መባ ይህ ነበረ።

66 በዐ​ሥ​ረ​ኛ​ውም ቀን የዳን ልጆች አለቃ የአ​ሚ​ሳዲ ልጅ አኪ​ያ​ዜር መባ​ውን አቀ​ረበ፤

67 መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤

68 ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤

69 ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤

70 ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤

71 ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የአ​ሚ​ሳዲ ልጅ የአ​ኪ​ያ​ዜር መባ ይህ ነበረ።

72 በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛ​ውም ቀን የአ​ሴር ልጆች አለቃ የኤ​ክ​ራን ልጅ ፋግ​ኤል መባ​ውን አቀ​ረበ፤

73 መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤

74 ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤

75 ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤

76 ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤

77 ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የኤ​ክ​ራን ልጅ የፋ​ግ​ኤል መባ ይህ ነበረ።

78 በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ቀን የን​ፍ​ታ​ሌም ልጆች አለቃ የዔ​ናን ልጅ አኪሬ መባ​ውን አቀ​ረበ፤

79 መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤

80 ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤

81 ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤

82 ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል፤

83 ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የዔ​ናን ልጅ የአ​ኪሬ መባ ይህ ነበረ።

84 መሠ​ዊ​ያው በተ​ቀባ ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ​ቆች ለመ​ሠ​ዊ​ያው መቀ​ደሻ ያቀ​ረ​ቡት መባ ይህ ነበረ፤ ዐሥራ ሁለት የብር ወጭ​ቶች፥ ዐሥራ ሁለት የብር ድስ​ቶች፥ ዐሥራ ሁለት የወ​ርቅ ጭል​ፋ​ዎች፤

85 እያ​ን​ዳ​ን​ዱም የብር ወጭት መቶ ሠላሳ ሰቅል፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ድስት ሰባ ሰቅል ነበረ፤ የዚ​ህም ዕቃ ሁሉ ብር በመ​ቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰቅል ነበረ።

86 ዕጣ​ንም የተ​ሞሉ ዐሥራ ሁለት የወ​ርቅ ጭል​ፋ​ዎች፥ እያ​ን​ዳ​ንዱ በመ​ቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን ዐሥር ዐሥር ሰቅል ነበረ፤ የጭ​ል​ፋ​ዎቹ ወርቅ ሁሉ መቶ ሃያ ሰቅል ነበረ።

87 የሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ከብት ሁሉ ከእ​ህሉ ቍር​ባን ጋር ዐሥራ ሁለት ወይ​ፈ​ኖች፥ ዐሥራ ሁለ​ትም አውራ በጎች፥ ዐሥራ ሁለ​ትም የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ነበሩ፤ የኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አውራ ፍየ​ሎች ዐሥራ ሁለት ነበሩ።

88 የደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከብት ሁሉ፥ ሃያ አራት ጊደ​ሮች፥ ስድ​ሳም አውራ በጎች፥ ስድ​ሳም አውራ ፍየ​ሎች፥ ስድ​ሳም ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበሩ። መሠ​ዊ​ያው ከተ​ቀባ በኋላ ለመ​ቀ​ደ​ሻው የቀ​ረበ ቍር​ባን ይህ ነበረ።

89 ሙሴም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን እር​ሱን ለመ​ነ​ጋ​ገር በገባ ጊዜ በቃል ኪዳኑ ታቦት ላይ ካለው ከስ​ር​የት መክ​ደ​ኛው በላይ ከኪ​ሩ​ቤ​ልም መካ​ከል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ ይሰማ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ይና​ገር ነበር።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች