Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 6:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እን​ዲሁ ስሜን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ይጠ​ራሉ፤ እኔም እባ​ር​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 “በዚህ ሁኔታ ስሜን በእስራኤላውያን ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እነርሱም ስሜን በእስራኤል ልጆች ላይ ያኖራሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ደግሞም እግዚአብሔር “በዚህ ሁኔታ ስሜን ጠርተው የእስራኤልን ሕዝብ ቢባርኩ፥ እኔም እነርሱን እባርካቸዋለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እንዲሁ ስሜን በእስራኤል ልጆች ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 6:27
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሊነጋ ጎሕ ቀድ​ዶ​አ​ልና ልቀ​ቀኝ።” እር​ሱም “ከአ​ል​ባ​ረ​ክ​ኸኝ አል​ለ​ቅ​ህም” አለው።


ያዕ​ቆ​ብም፥ “ስም​ህን ንገ​ረኝ” ብሎ ጠየ​ቀው። እር​ሱም፥ “ስሜን ለምን ትጠ​ይ​ቃ​ለህ? ድንቅ ነውና” አለው።


ለእ​ርሱ ለራሱ እን​ዲ​ሆን ሕዝ​ብን ይቤዥ ዘንድ ለእ​ርሱ ለራ​ሱም ታላቅ ስምን ያደ​ርግ ዘንድ አሕ​ዛ​ብ​ንና ሰፈ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን በመ​በ​ተን ከግ​ብፅ በተ​ቤ​ዠ​ኸው ሕዝ​ብህ ፊት ታም​ራ​ት​ንና ድን​ቅን ያደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ መራው እንደ ሕዝ​ብህ እንደ እስ​ራ​ኤል ያለ በም​ድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?


ያግ​ቤ​ጽም፥ “እባ​ክህ፥ መባ​ረ​ክን ባር​ከኝ፥ ሀገ​ሬ​ንም አስ​ፋው፤ እጅ​ህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እን​ዳ​ያ​ሳ​ዝ​ነ​ኝም ምል​ክት አድ​ር​ግ​ልኝ” ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ጠራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የለ​መ​ነ​ውን ሰጠው።


በስሜ የተ​ጠ​ሩት ሕዝቤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን አዋ​ር​ደው ቢጸ​ልዩ፥ ፊቴ​ንም ቢፈ​ልጉ፥ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም ቢመ​ለሱ፥ በሰ​ማይ ሆኜ እሰ​ማ​ለሁ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይቅር እላ​ለሁ፤ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም እፈ​ው​ሳ​ለሁ።


አንተ ጻድ​ቁን ትባ​ር​ከ​ዋ​ለ​ህና፤ አቤቱ፥ እንደ አላ​ባሽ ጋሻ ከለ​ል​ኸን።


አቤቱ፥ በሕ​ዝ​ብህ ፊት በወ​ጣህ ጊዜ፥ በም​ድረ በዳም ባለ​ፍህ ጊዜ፥


ለአ​ብ​ር​ሃ​ምም፥ ለይ​ስ​ሐ​ቅም፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ሁሉን እን​ደ​ሚ​ችል አም​ላክ ተገ​ለ​ጥሁ፤ ነገር ግን ስሜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ታ​ወ​ቀ​ላ​ቸ​ውም ነበር።


በስሜ የተ​ጠ​ራ​ውን ለክ​ብ​ሬም የፈ​ጠ​ር​ሁ​ትን፥ የሠ​ራ​ሁ​ት​ንና ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ሁሉ አምጣ” እለ​ዋ​ለሁ።


እን​ዳ​ን​ቀ​ላፋ ሰው፥ ያድ​ንም ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ችል ኀያል ስለ ምን ትሆ​ና​ለህ? አንተ ግን አቤቱ! በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ነህ፤ ስም​ህም በእኛ ላይ ተጠ​ር​ት​ዋል፤ አት​ር​ሳ​ንም።


እነሆ፥ መጥ​ቻ​ለሁ፤ እባ​ር​ካ​ለሁ፤ አል​መ​ለ​ስ​ምም፤


እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም፥ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”


በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ በሰ​ማ​ያዊ ስፍራ በመ​ን​ፈ​ሳዊ በረ​ከት ሁሉ የባ​ረ​ከን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


የም​ድር አሕ​ዛ​ብም ሁሉ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም በአ​ንተ ላይ እንደ ተጠራ አይ​ተው ይፈ​ሩ​ሃል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች