የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 33:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሙ​ሴና በአ​ሮን እጅ ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሰ​ፈ​ሩ​በት ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እስራኤላውያን በየነገዳቸው ተከፋፍለው በሙሴና በአሮን መሪነት ከግብጽ ወጥተው፣ በጕዞ ላይ ሳሉ የሰፈሩባቸው ቦታዎች እነዚህ ናቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሙሴና በአሮን ልጅ እየተመሩ በየሠራዊታቸው ሆነው ከግብጽ በወጡ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ያደረጉት ጉዞ ይህ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስራኤላውያን በየነገዳቸው ተከፋፍለው በሙሴና በአሮን መሪነት ከግብጽ ከወጡ በኋላ በየጊዜው የሰፈሩባቸውን ቦታዎች የሚያስረዳው ታሪክ ይህ ነው፦

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤልም ልጆች ጕዞ ከሙሴና ከአሮን ልጅ በታች በጭፍሮቻቸው ከግብፅ በወጡ ጊዜ እንዲህ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 33:1
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እጁ​ንም አነ​ሣ​ባ​ቸው። በም​ድረ በዳ ይጥ​ላ​ቸው ዘንድ፥


ዓለ​ቱን ይመታ ዘንድ ውኃ​ንም ያፈስ ዘንድ ይች​ላ​ልን? እን​ጀ​ራን መስ​ጠ​ትና ለሕ​ዝ​ቡስ ማዕ​ድን መሥ​ራት ይች​ላ​ልን?”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከራ​ምሴ ተነ​ሥ​ተው ወደ ሱኮት ሄዱ፤ ከጓዝ ጋር ካሉት ሌላ ስድ​ስት መቶ ሺህ ሰው የሚ​ያ​ህል እግ​ረኛ ነበረ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት ሁሉ በሌ​ሊት ከግ​ብፅ ምድር ወጣ።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣ​ቸው።


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን በዙ​ሪያ መን​ገድ በኤ​ር​ትራ ባሕር ባለ​ችው ምድረ በዳ መራ​ቸው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ትው​ልድ ከግ​ብፅ ምድር ወጡ።


እነ​ዚህ አሮ​ንና ሙሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ከግ​ብፅ ምድር ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አውጡ” ያላ​ቸው ናቸው።


ከግብጽ ምድር አውጥቼሃለሁ፥ ከባርነት ቤትም ተቤዥቼሃለሁ፥ በፊትህም ሙሴንና አሮንን ማርያምንም ልኬልህ ነበር።


ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ እንደ ተጓዙ የሰ​ፈ​ሩ​በ​ትን ጻፈ፥ እየ​ተ​ጓዙ ያደ​ሩ​በት ይህ ነው።


ሙሴ​ንና አሮ​ን​ንም ላክሁ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ስላ​ደ​ረ​ጉት ነገር ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ቀሠ​ፍ​ኋ​ቸው፤


ያዕ​ቆ​ብና ልጆቹ ወደ ግብጽ በገቡ ጊዜ ግብ​ጻ​ው​ያን አስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ላከ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ከግ​ብጽ አው​ጥ​ተው በዚህ ቦታ አኖ​ሩ​አ​ቸው።