Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 12:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ያዕ​ቆ​ብና ልጆቹ ወደ ግብጽ በገቡ ጊዜ ግብ​ጻ​ው​ያን አስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ላከ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ከግ​ብጽ አው​ጥ​ተው በዚህ ቦታ አኖ​ሩ​አ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ያዕቆብ ወደ ግብጽ ከገባ በኋላ፣ አባቶቻችሁ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ወደ እርሱ ጮኹ፤ እግዚአብሔርም የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር አውጥተው በዚህ ስፍራ እንዲኖሩ ያደረጉትን ሙሴንና አሮንን ላከላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ያዕቆብ ወደ ግብጽ ከገባ በኋላ፥ አባቶቻችሁ ጌታ እንዲረዳቸው ወደ እርሱ ጮኹ፤ ጌታም የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር አውጥተው በዚህ ስፍራ እንዲኖሩ ያደረጉትን ሙሴንና አሮንን ላከላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ያዕቆብና ቤተሰቡ ወደ ግብጽ ወርደው በዚያ ሲኖሩ ግብጻውያን የጭቈና ቀንበር ጫኑባቸው፤ የቀድሞ አባቶቻቸውም ርዳታ ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን ላከላቸው፤ እነርሱም ከግብጽ መርተው በማውጣት በዚህች ምድር እንዲሰፍሩ አደረጉአቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ያዕቆብና ልጆቹ ወደ ግብጽ በገቡ ጊዜ ግብጻውያን አስጨነቁአቸው፥ አባቶቻችሁም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን ላከ፥ አባቶቻችሁንም ከግብጽ አውጥተው በዚህ ቦታ አኖሩአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 12:8
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ያዕ​ቆ​ብም ወደ ግብፅ ወረደ፥ እር​ሱም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሞቱ።


እንደ ተጨ​ነ​ቁም ተመ​ለ​ከ​ታ​ቸው፥ ጸሎ​ታ​ቸ​ው​ንም ሰማ​ቸው፤


ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን አለ፥ “ሙሴ​ንና አሮ​ንን ያላቀ፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ከግ​ብጽ ምድር ያወጣ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክር ነው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ አወ​ጣሁ፤ ከግ​ብፅ ንጉሥ ከፈ​ር​ዖ​ንም እጅ፥ ከሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ች​ሁም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ እጅ አዳ​ን​ኋ​ችሁ’ አላ​ቸው።


ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ የማ​ል​ሁ​ላ​ቸ​ውን ምድር ለዚህ ሕዝብ ታወ​ር​ሳ​ለ​ህና ጽና፥ በርታ።


አባ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በግ​ብ​ፅም እጅግ ዘመን ተቀ​መ​ጥን፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም እኛ​ንና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን በደሉ።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣ​ቸው።


እነ​ዚህ አሮ​ንና ሙሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ከግ​ብፅ ምድር ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አውጡ” ያላ​ቸው ናቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰጠ፤ ወረ​ሱ​አ​ትም፥ ተቀ​መ​ጡ​ባ​ትም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች