የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 25:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ያንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰው ተከ​ትሎ ወደ ድን​ኳኑ ገባ። ሁለ​ቱ​ንም እስ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ውን ሰውና ምድ​ያ​ማ​ዊ​ቱን ሴት ሆዳ​ቸ​ውን ወጋ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መቅ​ሠ​ፍቱ ተወ​ገደ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እስራኤላዊውን ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ፤ ጦሩንም ወርውሮ እስራኤላዊውንና ሴቲቱን አጣምሮ ወጋቸው። ከዚያም በእስራኤላውያን ላይ የወረደው መቅሠፍት ተከለከለ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ያንንም የእስራኤልን ሰው ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ። እስራኤላዊውንም ሰውና ሴቲቱን ሁለቱንም ሆዳቸውን ወጋቸው። ከእስራኤልም ልጆች መቅሠፍቱ ተከለከለ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰውየውና ሴቲቱ ወዳሉበት ድንኳን ገባ፤ ሁለቱንም በአንድነት በጦር ወግቶ ገደላቸው፤ በዚህም ዐይነት እስራኤላውያንን በማጥፋት ላይ የነበረው መቅሠፍት ቆመ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ያንንም የእስራኤልን ሰው ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ። እስራኤላዊውንም ሰውና ሴቲቱን ሁለቱን ሆዳቸውን ወጋቸው። ከእስራኤልም ልጆች መቅሠፍቱ ተከለከለ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 25:8
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሳ​ኦ​ልን አጥ​ን​ትና የል​ጁን የዮ​ና​ታ​ንን አጥ​ንት፥ የተ​ሰ​ቀ​ሉ​ት​ንም ሰዎች አጥ​ንት በብ​ን​ያም በአ​ባቱ በቂስ መቃ​ብር አጠ​ገብ ቀበ​ሩ​አ​ቸው፤ ንጉ​ሡም ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ። ከዚ​ያም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ርን ሰማት።


በዚ​ያም ዳዊት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረበ። ሰሎ​ሞ​ንም በኋላ ዘመን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመረ፤ ያን​ጊዜ አነ​ስ​ተኛ ነበ​ርና። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ሀገ​ሪቱ የተ​ለ​መ​ነ​ውን ሰማ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ተከ​ለ​ከለ።


ዳዊ​ትም ኦር​ናን፥ “በላዩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ እሠራ ዘንድ ይህን የአ​ው​ድማ ስፍራ ስጠኝ፤ በሙሉ ዋጋ ሽጥ​ልኝ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ከሕ​ዝቤ ይከ​ለ​ከ​ላል” አለው።


ቃል ኪዳኔ ከእርሱ ጋር የሕይወትና የሰላም ቃል ኪዳን ነበረ፣ ይፈራ ዘንድም እነርሱን ሰጠሁት፣ እርሱም ፈራኝ፥ ከስሜም የተነሣ ደነገጠ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድን​ኳን የሚ​ነካ ሁሉ ይሞ​ታል። በውኑ ሁላ​ችን ፈጽ​መን እን​ሞ​ታ​ለን?”


“የካ​ህኑ የአ​ሮን ልጅ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ በቅ​ን​ዓቴ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቀን​ቶ​አ​ልና ቍጣ​ዬን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መለሰ፤ እኔም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በቅ​ን​ዓቴ አላ​ጠ​ፋ​ሁም።


ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሕዝ​ቦች፥ “እና​ንተ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ብዔል ፌጎ​ርን የተ​ከ​ተ​ሉ​ትን ሰዎ​ቻ​ች​ሁን ግደሉ” አላ​ቸው።


በላ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ተመ​ለሰ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ዔሜ​ቃ​ኮር ተብሎ ተጠራ።